የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ለሞሮኮው የአፍሪካ ዋንጫ የሚያደርገውን ዝግጅት ቀጥሏል
አሰልጣኝ ቤንጃሚን ዚመር የመጨረሻ ስብስባቸውን በመያዝ በዛሬው ዕለት በኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ መደበኛ ልምምዳቸውን አከናውነዋል።

ዳዊት ካሣው፣ ቸርነት ኡፋይሳ እና አቤኔዘር ዓለማየሁ ባሳለፍነው ሐሙስ ቡድኑን ሲቀላቀሉ ሁዜይፋ ሻፊ እና ቅዱስ ዳዊት ደግሞ ትናንት በመቀላቀል በዛሬው ዕለት ከቡድኑ ጋር ልምምዳቸውን አከናውነዋል።

የቀድሞው የቅዱስ ጊዮርጊስ አሰልጣኝ ሰርዮቪች ሚሉቲን “ሚቾ” በዛሬው የልምምድ መርሐ ግብር ላይ ተገኝተው ልምዳቸውን በማካፈል ቡድናችንን አበረታተዋል።

መረጃው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ነው

