ልደታ ክ/ከተማ ወደ 2019 የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ማሳደግ የቻለው አሰልጣኝ ሙሉጌታ ገ/ሥላሴ

ልደታ ክ/ከተማን ረጂም ዓመት በም/አሰልጣኝነት መሥራት የቻለው ሙሉጌታ ገ/ሥላሴ የተለያዩ የከፍተኛ ሊግ ዕድሎች ማግኘት ብችልም ከልደታ ክ/ከተማ አመራሮች ጋር በመነጋገር ክለቡን እንደተረከበና ለራሱ አጨዋወት ይሆኑኛል ብሎ የሚያስባቸውን ተጨዋቾች መርጦ ከሁሉም ቡድን ቀድሞ ወደ ልምምድ መግባቱን ተናግሯል።

በልምምድ ወቅትም በተጨዋቾች አቅም እና ክህሎት ላይ መነሻ በማድረግ ወደ ውድድር መግባቱን ገልጿል።

በክለቡ ያሉ ተጨዋቾች ባጠቃላይ በሚባል ደረጃ የመጫወት ዕድል እንደነበራቸውና ተቀራራቢ ችሎታ ደረጃ ላይ የሚገኙ ተጨዋቾችን መሰብሰቡ እንድሁም እያንዳንዱን ጨዋታ ትኩረት ሰጥተው መጫወታቸው ረጂም ጉዞው እንዲያደርግ እንደረዳው ገልጿል።

ክለባችን በዲሲፕሊን ረገድ አንድ ቤተሰብ ነበር የሚመስለው መከባበራችን ለዝህ ውጤት ዋናውን ድርሻ ይወስዳል ከክለቡ የሚደረግልን ድጋፍ አልነበረም ያ ተደምሮ ልደታ ክ/ከተማ ወደ ከፍተኛ ሊግ ሊያድግ ችሏል ለዝህ ለመጣው ውጤት ባጠቃላይ የክለቡ ኃላፊዎች እና የአሰልጣኝ ቡድን አባላትን ለማመስገን እወዳለሁ በማለት ተናግሯል።

በ2019 የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ልደታ ክ/ከተማ ላለመውረድ የሚጫወት ቡድን ሳይሆን በሊጉ ተፎካካሪ ቡድን ይዞ እንደሚቀርብና ለዝህም ደግሞ የሚመጥኑ ተጨዋቾች ክለቡ ውስጥ ይገኛሉ በተጨማሪ ለከፍተኛ ሊግ የሚሆኑ ተጨዋቾችን ክለቡ ውስጥ ቀላቅዬ የተሻለ ወደ ፕሪምየር ሊግ የሚያድግ ቡድን ሰርቼ እመጣለሁ ሲል ዋና አሰልጣኝ ሙሉጌታ ገ/ሥላሴ ገልጿል።

ልደታ ክ/ከተማ በኢትዮጵያ ሊግ አንድ ምድብ ሀ አንድ 31 ጨዋታ በማድረግ 20 ጨዋታ በማሸነፍ አንድ ጨዋታ ብቻ ተሸንፎ 70 ነጥቦችን በመሰብሰብ ወደ 2019 የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ማደጉን ቀድሞ ያረጋገጠ ክለብ ሲሆን በማጠቃለያ ውድድር የስፖርታዊ ጨዋነት ዋንጫ በማሸነፍ 2ኛ ደረጃ ይዞ ማጠናቀቅ ችሏል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *