ይርጋጨፌ ቡናን ወደ 2019 የኢትጵያ ከፍተኛ ሊግ ማሳደግ የቻለው አሰልጣኝ ኢዮብ ዋቤ

የነበረው ጉዞ በጣም ረጂም ጉዞ ነው ብዙም በማይመቹ ሜዳዎች ነው ሁለቱንም ዙር ጨዋታዎችን ያደረግነው በበርካታ ውጣ ውረድ ውስጥ አልፈን የምንፈልገውን ውጤት አስመዝግበናል ሲል ተናግሯል።

ይርጋጨፌ ቡና ከዝህ በፊት ብዙ ታላላቅ ተጨዋቾችን ያፈራ ቡድን ነው ዞኑ ወደ ከፍተኛ ሊግ እንድናግድግ የተሻለ ሥራዎችን ሰርቷል ለዛም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ወደ ከፍተኛ ሊግ ያደግነው የጥሎ ማለፍ ጨዋታ ተጫውተን ነው እጅግ ከባድ ነበር ጨዋታው ግን በፈጣሪ እርዳታ ወደ ከፍተኛ ሊግ አድገናል ለዝህም ከጎኔ ለነበሩ የአሰልጣኝ ቡድን አባላት ፣ ለዞኑ አመራሮች እና ለክለቡ ተጨዋቾችን ለማመስገን እፈልጋለው ሲል ገልጿል።

ዋና አሰልጣኝ ኢዮብ ዋቤ በሚቀጥለው ዓመት ክለቡን ወደ 2020 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ለማሳደግ የተሻለ ቡድን ይዘን እንቀርባለን የአከባቢው ባለሀብት እንድሁም አመራሮች ለዝህ ከወድሁ ሥራ እየሰሩ እንደሚገኙ ገልፀዋል።

አሰጋኸኝ ጉዬ የይርጋጨፌ ቡና እግር ኳስ ክለብ ሥራ አስኪያጂ እንደገለፁት በመጀመሪያ ዝግጅታቸውን አርፍደው እንደጀመሩና የዋና አሰልጣኝ ቅጥር ተጨዋቾችም በአጭር ጊዜ መሰባሰባቸው ገልፀው ከሁለት ዓመት በፊት ክለቡ ከከፍተኛ ሊግ ይርጋጨፌ ቡና ሲወርድ ከፍተኛ የበጀት እጥረት ዋነኛው የክለቡ ውድቅ ምልክት እንደነበረ ገልፀው አሁን ግን ክለቡ ከቦርድ ጀምሮ እንደ አዲስ በመዋቀሩ የተሻለ ውጤት መቷል ሲል ገልጾ በሚቀጥለው ዓመቱ ክለቡ ወደ ፕሪምየር ሊግ እንዲያድግ ከወድሁ ዞኑም የተለያዩ ሥራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ ተናግሯል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *