ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በተገኙበት ለጋሞ ጨንቻ የወንዶች እግር ኳስ ቡድን እና ለፕሪሜር ሊግ ተሳታፊዎቹ ለይርጋ ጨፈ የሴቶች እግር ኳስ ቡድን የውቅናና የሽልማት ስነስርዓት ተካሂዷል።


የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ለሁለቱም ክለቦቹ ማመላለሻ እንዲሆን አውቶቢስ ለየክለቦቹ የአንድ ሚሊየን ብር ድጋፍ ማድረጉን ገልፀው በቀጣይ አስፈላጊው ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል።
በመርሃ ግብሩ መልዕክት ያስተላለፉት ርዕሰ መስተዳድሩ የሁለቱም ክለብ ስኬታማነት ብዙ የተመቻቸ ነገር በሌለበት በልፋት ፣ በትጋት እና በፅናት የተገኘ ውጤት መሆኑን ገልፀው ለሁለቱም ክለቦች በክልሉ መንግስት ስም ምስጋና አቅርበዋል።

በሴቶች ክለብ ውድድር እምብዛም ትኩረት ባልተሰጠበት የይርጋጨፌ ሴቶችን ቡድን በፅናት ፈተናዎችን በመቋቋም ወደ ፕሪሜርሊጉ በመቀላቀል ላበረከቱት አስተዋፅኦ ምስጋና አቅርበዋል።

ክልሉን በመወከል በሀገር አቀፍ ውድድሮች የሚሳተፉ ክለቦች መበራከት በክልሉ የስፖርቱን ዘርፍ በማነቃቃትና ለዘርፉ ዕድገት የሚደረገውን ጥረት ከማገዝ ባለፈ ብቃት ያላቸው ስፖርተኞችን ለማፍራት ለሚደረገው ጥረት ውጤታማነት ፋይዳው የጎላ ነው።

