መቐለ 70 እንደርታ ቦዲቲ ከተማን ካሸነፈ በኃላ የሁለቱ ቡድኖች አሰልጣኞች ምን አሉ ?

የቦዲቲ ከተማ አሰልጣኝ አዲሱ ዶይሶ

ጨዋታው ጥሩ ነበር በልጆቼ በጣም ኮርቻለው በመጀመሪያ አጋማሽ ጎል ማስቆጠር የምንችልበትን አጋጣሚ መጠቀም አልቻልንም በዛ ምክንያት ዋጋ ከፍለናል ልጆቼ ግን ማድረግ ያለባቸውን አቅማቸው የሚችለው ነገር በሙሉ ሜዳ ላይ አድርገዋል ለዛ ማመስገን እፈልጋለው ሲል ገልጿል።

የተጫወትነው ከመቐለ 70 እንደርታ ነው ትልቅ ክለብ ነው ልጆቻችንም እንዳያችሁ ከሆነ አቅም ያላቸው ናቸው ጥሩ ነገር ሜዳ ላይ አሳይተዋል የተቆጠሩ ጎሎች ከተከላካይ መስመር ነው በማለት ተናግሯል።

ወደ ጨዋታው ለመመለስ አጥቅተን ለመጫወት ጥረት አድርገናል ጎልም አስቆጥረናል ነገር ግን እነሱም ውጤት ይፈልጉ ስለነበር ሰዓት መግደል ጋር ተያይዞ ከጨዋታ እንቅስቃሴ አውጥተውናል በማለት ተናግሯል።

ስለ ከፍተኛ ሊግ መጨረሻ ጨዋታ………

እኛ ከጀርባችን ብዙ ችግሮች አሉብን ከፋይናንስ ጋር ተያይዞ ነገር ግን ልጆቹ የሚችሉትን አድርገው እስከመጨረሻ ታግለዋል ከሶሎዳ ዓድዋ ጋር ያለው ጨዋታ ማሸነፍ ብቻ ሳይሆን አሸንፈንም የሌሎች ክለቦች ውጤትም እንጠብቃለን እግዝአብሔር የፈቀደው ነው የሚሆነው የሚመጣውን ውጤት በፀጋ እንቀበላለን ሲል ገልጿል።

የመቐለ 70 እንደርታ አሰልጣኝ ፀጋዬ ኪ/ማርያም

ጨዋታው የጥሎ ማለፍ ጨዋታ ነው ቀድሞ ጎል ያስቆጠረው ቡድን በራስ መተማመኑ ከፍ ያደርጋል በሊግ ደረጃ የአንድ ዕርከን ልዩነት አለን በዛ ምክንያት የሰጡት ግምት ከፍ ያለ ነው ልጆቻችን የመጀመሪያ 20 ደቂቃ ወደ ጨዋታ መግባት አልቻሉም በዛ ምክንያት በጎል ቀድመውናል በጎል ከተቀደምክ ደግሞ ተጋጣሚው ቡድን እየተነሳሳ ይሄዳል በዛም ቡድኑ የራስ መተማመኑ ወርዶ ነበር በማለት ተናግሯል።

በሁለተኛ አጋማሽ በተጨዋቾች ቂያሪ አድርገናል ሱሌይማን ሀሚድ ለጨዋታ ብቁ መሆን አልቻለም ያም ብሆን ግን አጨዋወት መንገድ ብዙም አልቀየርንም ግን በተቀየሩ ተጨዋቾች ለውጥ ለማምጣት ሞክረና ሲል ተናግሯል።

ጥሎ ማለፍ አስቼጋሪ ጨዋታ በዕለቱ የተሻለው ቡድን ነው የሚያሸንፈው ያን ያህል የተጋነነ ነገር ባይኖርም ግን ተጋጣሚያችን ቦዲቲ ከተማም ጥሩ ነገር ነው ያሳየው በሁለተኛ አጋማሽ የአማካይ ተጨዋች ቁጥር በማብዛት የተሻለ የኳስ ቁጥጥር እንድኖር ማድረግ ችለናል ሲል ገልጿል።

መቐለ 70 እንደርታን በፕሪሚየር ሊጉ ለማቆየት እየተደረገ ያለው እንቅስቃሴ በተመለከተ……………………..

ከዝህ በኋላ ያሉ 10 የሊግ ጨዋታዎች እንደዛረው የጥሎ ማለፍ ጨዋታ ናቸው ከመጨረሻ ሁለት ጨዋታ 6 ነጥብ ማሳካት ችለናል 5 ግቦችን አስቆጥረናል አንድ ጎል ተቆጥሮብናል ቀጣይ ያሉትን ጨዋታዎችንም በትኩረት ካልተጫወትን ዋጋ ሊያስከፍለን ይችላል ከባድ የቤት ሥራ ይጠብቀናል ሲል ገልጿል።