የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ምድብ ለ 19ኛ ሳምንት ሁለተኛ ቀን ውሎ !

ደሴ ከተማ ወሳኝ ድል አስመዝግቧል

የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ምድብ ለ19ኛ ሳምንት ሁለተኛ ቀን የ3:00 ሰዓት ጨዋታ ደሴ ከተማ አዲስ አበባ ከተማን 2 ለ 1 በማሸነፍ ከመሪው ሀላባ ከተማ ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ አንድ ማጥበብ ችሏል።

በሀዋሳ አርቴፊሻል ስታዲየም አዲስ አበባ እና ደሴ ከተማ ያደረጉት ጨዋታ 5ኛ ደቂቃ ላይ ለአዲስ አበባ ከተማ ቅዱስ ተስፋዬ ግብ መሪ መሆን ብችሉም 13ኛ ደቂቃ ላይ ፈጣኑ የመስመር አጥቂ ቢላል ገመዳና በ29ኛ ደቂቃ በተከላካዩ በጋሻው ክንዴ አማካኝነት ባስቆጠራቸው ሁለት ግቦች ደሴ ከተማ ጨዋታውን አሸንፎ መውጣት ችሏል።

ሀላባ ከተማ በ35 ነጥብ ምድቡን እየመራ ሲገኝ ደሴ ከተማ በ34 ነጥብ እየተከተለ ይገኛል ።

5:00 ሰዓት ላይ በተካሄደው ጨዋታ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ከ አዲስ ከተማ ክ/ከተማ 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቋል።

አዲስ ከተማ ክ/ከተማ በ21ኛ ደቂቃ ቶማስ ቶይቶ ባስቆጠረው ጎል 1ለ0 መምራት ብችልም 45ኛ ደቂቃ አቤኔዘር ማቴዎስ ለንፋስ ስልክ ላፍቶ ጎል አስቆጥሮ ጨዋታው 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት ተጨማሪ ግብ ሳይቆጠር በዛው ውጤት መጠናቀቅ ችሏል።      

ውጤቱን ተከትሎ አዲስ ከተማ ክ/ከተማ በ23 ነጥቦች 5ኛ ደረጃ ላይ ሲገኝ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ በ18 ነጥብ 9ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

8:00 ሰዓት በተካሄደው ጨዋታ ቦዲቲ ከተማ ከሱሉልታ ክ/ከተማ ያደረጉት ጨዋታ በቦዲቲ ከተማ 1ለ0 አሸናፊነት መጠናቀቅ ችሏል።

ሁለቱ ቡድኖች ለመሸናነፍ ብርቱ ፉክክር ያደረጉ ሲሆን በመጀመሪያ አጋማሽ ሁለቱም ቡድኖች ግብ ለማስቆጠር ሲቸገሩ ተስተውሏል።

ሁለተኛ አጋማ መደበኛ 90 ደቂቃ ሊጠናቀቅ 8 ደቂቃዎች ሲቀሩ ቦዲቲ ከተማዎች ያገኙትን የግብ ማግባት ዕድል 82ኛ ደቂቃ ላይ ካሳሁን በለጠ በማስቆጠር ጨዋታው ቦዲቲ ከተማ አሸንፎ እንድወጣ ማድረግ ችሏል።

ውጤቱን ተከትሎ ቦዲቲ ከተማ ደረጃውን ማሻሻል ባይችልም ነጥቡን 17 በማድረስ 10ኛ ደረጃ ላይ ሲገኝ ሽንፈት ያስተናገደው ሱሉልታ ክ/ከተማ በ2 ነጥቦች ቦዲቲ ከተማን በመብለጥ በ19 ነጥብ 8ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ምድብ ለ 19ኛ ሳምንት ነገ 4:00 ሰዓት ቢሾፍቱ ከተማ ከ ደብረ ብርሃን ከተማ በሚያደርጉት ጨዋታ ፍፃሜውን ያገኛል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *