የኢትዮጵያ ሴት እግር ኳስ አሰልጣኞች የሙያ ማህበር ከኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ በጋራ ያዘጋጀው የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና ዛሬ ተጠናቀቀ።

በኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ እና በኢትዮጵያ የሴቶች እግር ኳስ አሰልጣኞች የሙያ ማህበር አባላት ሰኔ 11/2019 እና 12/2018 ዓ.ም ለሁለት ተከታታይ ቀናት በተለያዩ ርዕሶች ላይ ሲሰጥ የቆየውን የተግባርና የንድፍ ሀሳብ የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና ተጠናቀቀ።

ያለፉትን ሁለት ተከታታይ ቀናት በአዳማ ከተማ ሲካሄድ የነበረው የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና አካዳሚው ከተሰጡት ተልዕኮዎች ውስጥ ለሀገሪቱ ስፖርት ሙያተኞች በዳሰሳ ጥናት በመለየት የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና መስጠት ሲሆን በዚሁ መሰረት አካዳሚው በየደረጃው ላሉ ባለሙያዎች  በርካታ ስልጠና መስጠቱ የሚታወስ ሲሆን አሁንም ለኢትዮጰያ የሴቶች ፕሪሚየር ሊግ እና ለኢትዮጵያ ሴቶች ከፍተኛ ሊግ አሰልጣኞች በጨዋታ ታክቲክ፣ በጨዋታ አስተዳደር እና በሌሎችም ርዕሶች ላይ ስልጠና ሰጥቷል።

በስልጠና መድረኩ የመጀመሪያ ቀን የአካዳሚው የአካዳሚው የትምህርት ስልጠናና ውድድር ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ደሳለኝ በላይ በመገኘት መልክት አስተላልፈዋል።

በስልጠናው የአካዳሚው የአትሌቶች ትምህርት እና ስልጠና መሪ ስራ አስፈፃሚ አሰልጣኝ ፍቃዱ ከበደ አካዳሚው ከምስረታው ጀምሮ ያሳለፈውን የስኬታማነት ጉዞ፣ አሰልጣኝ ማህደር እንየው የእግር ኳስ አካል ብቃት እና ታክቲክ አንዲሁም አሰልጣኝ ሀብታሙ ዳዲ የእግር ኳስ ጨዋታ አስተዳደር በሚሉ ርዕሶች ላይ ትምህርታዊ ስልጠና ሰጥተው በስልጠናው ተሳታፊዎች ሙያዊ ሀሳብ አስተያየት እና ጥያቄዎች ተነስተው የሚመለከታቸው አካላት ምላሽ ሰጥተውበታል።

ተሳታፊዎች በስልጠናው እጅግ መደሰታቸውን በመግለፅ አካዳሚው ለኢትዮጵያ የሴቶች እግርኳስ ዕድገት እየሰራ ያለው ስራ በጣም ሊመሰገን እንደሚገባው፣ ሀገርን በትልቅ ደረጃ ሊያገለግሉ የሚችሉ ተተኪዎችን በተግባር ማፍራት የቻሉ አቅም ያላቸው ቅን አሰልጣኞች እንዳሉት፣ ከአካዳሚው የሚወጡት ተጨዋችች ጥራት ያላቸው መሆናቸውን፣ እና ሌሎችንም በርካታ ጉዳዮችን በአዎንታዊነት ያነሱ ሲሆን አካዳሚው እና ማህበሩ የመግባቢያ ሰነድ መፈራረም ቢችሉ፣ አካዳሚው የራሱን የካምፕ ውድድር ማዘጋጀት ቢችል ፣ መሰል ስልጠናዎችን ለማህበሩ መስጠቱን አጠናክሮ እንዲቀጥል ሲሉ አበክረው ጠይቀዋል።

በመጨረሻም የአካዳሚው የስፖርት ባለሙያዎች ልማት መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ በቃኝ አበራ መድረኩን ሲያጠቃልሉ ባስተላለፉት መልዕክት አካዳሚው ከተሰጡት ተልዕኮዎች ውስጥ አንዱ በሆነው ለሀገሪቱ ስፖርት ሙያተኞች በዳሰሳ ጥናት በመለየት በየደረጃው ላሉ ባለሙያዎች በርካታ ስልጠና መስጠቱን እና እየሰጠ እንደሚገኝ በማስታወስ በተመሳሳይ ለኢትዮጵያ የሴቶች እግር ኳስ አሰልጣኞች የሙያ ማህበር አባላትም ስልጠና በመስጠታችን ደስተኛ ነን ያሉ ሲሆን አያይዘውም የተሰጡንን አስተያየቶች እንደ ግብአት ወስደን ከማህበሩ ጋር ያለንን ግንኙነት አጠናክረን እንቀጥላለን በማለት የስልጠና መድረኩ ተጠናቋል።

በመጨረሻም የሙያ ማህበሩ አካዳሚው በኢትዮጵያ የሴቶች እግርኳስ ዕድገት ላይ እየሰራ ላለው ስራ እና ስልጠናውን ለሰጡ አሰልጣኞች የማህበሩ ፕሬዝዳንት አሰልጣኝ ብርሃኑ ግዛው የእውቅና ሰርተፍኬት አበርክተዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *