ወላይታ ድቻ አንድ ተጨዋች ለማስፈረም ከስምምነት ላይ ሲደርስ የአንድ ነባር ተጨዋች ውል ለማራዘም ከስምምነት ላይ ደርሷል !

የጦና ንቦቹ የተከላካዩን ውብሸት ክፍሌን ኮንትራት ሲያራዝሙ አዲስ ተጫዋችም ወደ ስብስባቸው ለመቀላቀል ከስምምነት ላይ ደርሰዋል!

ከዝህ ቀደም በወላይታ ድቻ ተስፋ ቡድን ተጫውቶ ካሳለፈ በኃላ በከፍተኛ ሊግ ፡ቦዲቲ ከተማ እና አዲስ አበባ ከተማ በመጫወት ካሳለፈ በኃላ ዳግም ወደ ወላይታ ድቻ የተመለሰው የመሃል ተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ውብሸት ክፍሌ ለቀጣዮቹ ሁለት ተጨማሪ ዓመታት ከቡድኑ ጋር ለመቆየት ከስምምነት ላይ ደርሷል ።

ቡድኑን አዲስ የተቀላቀለው ከዝህ ቀደም በከፍተኛ ሊግ ቤንች ማጂ ቡና ተጫውቶ ካሳለፈ በኃላ ወደ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በመቀላቀል የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ሻምፒዮን መሆን የቻለውና ከዛም በአርባ ምንጭ ከተማ በግሉ ጥሩ ጊዜን ያሳለፈው ኤፍሬም ታምራት በሁለት ዓመት ኮንትራት ወላይታ ድቻን ለመቀላቀል ከስምምነት ላይ ደርሷል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *