ጉለሌ ክ/ከተማን ወደ ፕሪሚየር ሊግ ያሳደገው አሰልጣኝ አሸናፊ ለሻ

ከካባ ሜዳ ጀምሮ እስከ ፕሪሚየር ሊግ የጉለሌ ክ/ከተማ እንስት ቡድን ዋና አሰልጣኝ አሸናፊ ለሻ ስለ ውድድር ዓመቱ ተከታዩን ሐሳብ ሰጥቷል።

ጉለሌ ክ/ከተማ በርካታ ተጨዋቾችን ለከፍተኛ ሊግ እንድሁም ለፕሪሚየር ሊግ ክለቦች ግብዓት በመሆን የሚያገልግል ቡድን እንደነበርና በ2014 ምስረታውን በማድረግ የአዲስ አበባ ሻምፕዮን በመሆን በ2015 ከፍተኛ ሊግ መቀላቀሉንና ሶስትት ዓመታት ቆይታ በከፍተኛ ሊግ ካደረገ በኃላ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ማደጉን ገልጿል።

የመጀመሪያውን ዙር ሀዋሳ ከተማ ጥሩ ውድድር ጊዜ ነበር ያሳለፍነው ሰበታ ስታዲየም ከመጣን በኃላ በነበረው ቆይታ ቀጥታ ከአርቴፊሻል ሜዳ ወደዝህ ሜዳ ከመጣን በኃላ ሜዳው ለመላመድ ትንሽ ተቸግረን ነበር ሲል ዋና አሰልጣኝ አሸናፊ ለሻ ተናግሯል።

ስለሚቀጥለው ዓመት በፕሪሚየር ሊግ ሰለሚኖረው ቆይታ ውስን ፈተናዎች ልገጥሙን ይችላሉ ነገር ግን ስር ነቀል ለውጥ አምጥተን ከታችም በርካታ ታዳጊዎች አሉ ለዋናው ቡድን ግብዓት የሚሆኑ ተጨዋቾች ስላሉን ያን ያህል እንቸገራለን ብዬ አላስብም በማለት ገልጿል።

በመጨረሻም አሸናፊ ለሻ የጉለሌ ክ/ከተማ አመራሮችን ፣ የክለቡን ተጨዋቾ ፣ የአሰልጣኝ ቡድን አባላት እንድሁም የሽሮ ሜዳ ህዝብ ከጎኔ ነበሩ ለዝህ ውጤትም አስተዋጾ ነበራቸው በማለት ምስጋናውን አቅርቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *