ጥሩነሽ ዲባባ አካዳሚን ወደ ኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ያሳደገው አሰልጣኝ ሰለሞን ገለታ

ከዝህ ቀደም በአምቦ ጎል ፕሮጀክት ቆይታ ማድረግ የቻለውና በመጀመሪያ ዓመት ጥሩነሽ ዲባባ አካዳሚ በሴቶች ከፍተኛ ሊግ 4ኛ ደረጃ ይዞ እንዲያጠናቅቅ ማድረግ የቻለው ዋና አሰልጣኝ ሰለሞን ገለታ ከዳጉ ስፖርት ጋር ቆይታ አድርጓል።

በወንዶች በረከት ደስታን ፣ ብዙዓየሁ ሰይፌን ፣ ጌቱ ኃይለማሪምን ፣ ፉዓድ ኢብራሒምን ፣ አማኑኤል አድማሱን ፣
ገለታ ኃይሉ  እና መኮንን መርደኪዮስን ጨምሮ በርካታ ተጨዋቾችን ያፈራው ጥሩነሽ ዲባባ አካዳሚ በሴቶች ወደ ፕሪሚየር ሊግ አድጓል።

ቀድመን ወደ ፕሪሚየር ሊግ ማደጋችንን ብናረጋግጥም ግን ፉክክሩ እጅግ ከባድ ነበር ወጪና ወራጅም እስከ መጨረሻ ሳምንት ድሬስ ያልታወቀበት ነበር ጥሩነሽ ዲባባ አካዳሚ ለውድድሩ ጠንካራ ዝግጅት አድርገን ጠንካራ ተፎካካሪ ሆነን ቀርበን አምና 4ኛ ደረጃ ይዘን አጠናቀቀናል በዘንድሮ ዓመት ያሉብንን ችግሮች ቀርፈን ሻምፕዮን መሆን ችለናል ሲል ገልጿል።

ፕሪሚየር ሊጉ ላይ ስለሚኖረው ቆይታ

በኢትዮጵያ ሴቶች እግር ኳስ 90% የአካዳሚ ውጤቶች ናቸው የኛም ውጤት የዛ ማሳያ ነው አሁን ያሉ ተጨዋቾች ተመራቂዎች ናቸው ነገር ግን እየተተካ ስለሚሄድ ብያንስ ሊጉ ላይ ተፎካካሪ ሆኖ የሚቂይ ቡድን እንሰራለን ሲል ተናግሯል።

በመጨረሻም አሰልጣኝ ሰለሞን ገለታ ሁሉም ነገር የሆነው በፈጣሪ እገዛ ነው ከዛ በመቀጠል ግን የአትሌት ጥሩነሽ ዲባባ አካዳሚ ሠራተኞች ፣ የክለቡን ተጨዋቾ እና የአሰልጣኝ ቡድን አባላት እንድሁም የሰበታ ደጋፊ ኳስ ወዳድ ነው ኳሱን ብቻ አይተው ስለደገፉን ከልብ አመሰግናለሁ ሲል ምስጋናውን አቅርቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *