የኢትዮጵያ ሊግ አንድ የ2018 የውድድር ዘመን ከመጀመሩ አስቀድሞ ለጨዋታ አመራሮች የሚሰጠው የአካል ብቃት ምዘና በዛሬው ዕለት በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ተካሂዷል።
23 ዳኞች እና 33 ረዳት ዳኞች በምዘናው ላይ ተሳታፊ የሆኑ ሲሆን 18 ዳኞች እና 24 ረዳት ዳኞች ምዘናውን ማለፍ ችለዋል።
ከምዘናው በኋላ በሶራምባ ሆቴል በተሻሻሉ የጨዋታ ህጎች ዙርያ የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና የተሰጠ ሲሆን በነገው ዕለትም ስልጠናው ቀጥሎ ፍጻሜውን የሚያገኝ ይሆናል።










