ቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ አራት የውጪ ሀገር ዜግነት ያላቸው ተጨዋቾችን ውደ ስብስባቸው ቀላቅለዋል።
31 ጨዋታዎችን አድርጎ 39 ነጥቦችን በመሰብሰብ 12ኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ቅዱስ ጊዮርጊስ አራት አዳዲስ ተጨዋቾች አስፈርሟል።

የመጀመሪያ ፈራሚ የ23 ዓመቱ ጋናዊው ተከላካይ ኬልቪን ኤዶ ዶሴህ ሲሆን በአልባኒያ ዋናው ሊግ ተጫውቶ ያሳለፈ የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ነው።
ሁለተኛው አይቮሪኮስታዊው የ29 ዓመት አማካይ ስፍራ ተጨዋች ሲሆን ካርተር በአይቮኮስቱ አሴክ ሚሞሳስን ጨምሮ በኮንጎ ፣ ቤሩትና ኦማን ሊጎች መጫወት ችሏል ፡፡

ሶስተኛው ክሪስት ቶሉንጋ የኮንጎ ብራዛቪል ተወላጅ የሆነው የ20 ዓመት ወጣት የአጥቂ ስፍራ ተጨዋች ሲሆን ለሀገሩ ከ23 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ተሰልፎ መጫወት የቻለ ሲሆን ለሀገሩ ክለብ ዲያብሌስ ፣ ኖይሪስና ለአልጄሪያው ፓራዱ ክለቦች ተጫውቶ ማሳለፍ ችሏል፡፡
አራተኛው አልፍሬድ ሜንሳህ የ26 ዓመቱ ጋናዊው የአጥቂ ስፍራ ተጨዋች ሲሆን በአልባኒያ ፣ በኮሶቮ እና በጋና ፕሪምየር ሊግ ለተለያዩ ክለቦች ተጫውቶ ማሳለፍ ችሏል፡፡


