ስለ ዱራሜ ከተማ እና ወልቂጤ ከተማ
በኢትዮጵያ ሊግ አንድ 2018 የውድድር ዓመት መርሐ-ግብር ይፋ የተደረገ ሲሆን ዱራሜ ከተማ እና ወልቂጤ ከተማ መርሐ ግብሩ ላይ ለምን አልተካተቱም።
ያልተካተቱበት ምክንያት ምንድነው?
ሁለቱም ቡድኖች የሊግ አንድ መመዝገቢያ ክፊያ መፈፀም የቻሉ ቢሆንም አምና ከተጨዋቾች ደመወዝ ክፊያ ጋር በተያያዘ የክለብ ላይሰንስ ፍቃድ ማግኘት አልቻሉም ።
ዳጉ ስፖርት በክለቦቹ ዙሪያ ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ባደረገው ማጣራት የወረቀት ስራቸው ሲጨርሱ መርሐ-ግብር ላይ እንደሚካተቱ ከሊግ አንድ ውድድር ባለሙያዎች አረጋግጠናል።
ክለቦቹስ በምን ሁኔታ ላይ ይገኛሉ?
ዱራሜ ከተማ ዛሬ የተጨዋች ምልመላ መርሐ-ግብር ከ4:00 ሰዓት ጀምሮ ማከናወኑን ያረጋገጥን ሲሆን ወልቂጤ ከተማም ዝግጅት ማድረግ መጀመሩን ከቅርብ መረጃ ምንጭ ሰምተናል።

