የጋሞ ጨንቻ እግር ኳስ ክለብ መሥራች የሆነው ወጣቱ አሠልጣኝ ማቴዎስ ለማ ክለቡን ከከፍተኛ ሊግ ወደ ፕሪምየር ሊግ አሳደገ!

አሰልጣኝ ማቴዎስ ለማ የጋሞ ጨንቻ እግር ኳስ ክለብ መስራች ከመሆኑም በላይ ክለቡን ከዞን ሻምፒዮና ፣ ክልል ክለቦች ሻምፒዮና ፣ ኢትዮጵያ አንደኛ ሊግ ፣ ኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ እና ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ማሳደግ የቻለ አሠልጣኝ በመሆን ታሪክ ሰርቷል ።

👉ወደ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በማደጉ ስለተሰማው ስሜት…………….

እኔ ቃል የለኝም እግዝአብሔር በብዙ ረድቶኛ የሚገርሙ ልጆች ሰቶኛል በብዙ ነገር የሚታገሱ ዛሬ ልዩ ቀን ነው በተለይም ደግሞ ለጋሞ ህዝብ እንድሁም ለደቡብ ኢትዮጵያ ምክንያቱም ተፅኖ የሚፈጥር ክለብ ነው ጋሞ ጨንቻ ለመላው ኢትዮጵያ እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እፈልጋለው ሲል ተናግሯል።

👉ስለ ቀጣይ ዓላማ. ……………

ዓላማችን ሁልጊዜም በርትቶ መሥራት ነው ትጋት ነው ነገ መልካም እንድምሆን እያሰብን ወደፊት መቀጠል ነው የክለቡ ዋናው ዓላማ በአፍሪካ መድረክ ተሳታፊ ክለብ ሆኖ የማየት ፍላጎት እንዳለው ተናግሯል።

👉የድል ምስጥር……………..

የክለቡ የድል ምስጥር የተጨዋቾች አንድነት እና ጠንካራ የቡድኑ መንፈስ የስኬታቸው ምስጢር እንደሆነ ዋና አሰልጣኙ ማቴዎስ ለማ ገልፀዋል፡፡

የክለቡ ዋና አሰልጣኝ ማቴዎስ ለማ እንዳሉት ጋሞ ጨንቻ ቀደም ሲል የጨንቻ ከተማ በሚል ስያሜ ተመስርቶ በርካታ የእግር ኳስ ክዋክብትን ማፍራ የቻለ ሲሆን በ2005 ዓ.ም በአዲስ መልከ ተመሥርቶ በ2009 ዓ.ም ብሔራዊ ሊግ (አንደኛ ሊግ) መቀላቀል የቻለ መሆኑን አስታውሰው በ2009 ዓ.ም በከፍተኛ ሊጉ መሳተፍ የጀመረበትም ወቅት እንደሆነም አስረድተው በአንደኛ ሊግ አራት ዓመታትን ቆይታ የነበረው ጋሞ ጨንቻ በከፍተኛ ሊጉ 6 ዓመት ካስቆጠረ በኋላ በ2018 ወደ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ማደግ ችሏል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *