የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ምድብ ለ 20ኛ ሳምንት ሀላባ ከተማ ወደ ፕሪምየር ሊግ ሲያድግ አዲስ አበባ ከተማ መውረዱን አረጋጧል ።
የኢትዮጵያ የከፍተኛ ሊግ ምድብ ለ 20ኛ ሳምንት ጨዋታ በሀዋሳ አርቴፊሻል ስታዲየም እየተደረጉ የሚገኙ ሲሆን አዲስ አበባ ከተማ ወደ 2009 የኢትዮጵያ ሊግ አንድ መውረዱን አረጋግጧል ።
20ኛ ሳምንት የመጀመሪያ ጨዋታ አዲስ አበባ ከተማ ከቦዲቲ ከተማ ጋር ያደረጉት ጨዋታ 2ለ2 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቋል።
አዲስ አበባ ከተማ ጨዋታውን 2-0 እየመራ የመጀመሪያ አጋማሽ ማጠናቀቅ የቻለ ሲሆን ብሩክ ብርሃኑ እና ቸርነት ኦርጂኖ ጎሎችን ያስቆጠሩ ተጫዋቾች ናቸው።
በሁለተኛው አጋማሽ ተሻሽሎ የቀረበው ቦዲቲ ከተማ በቴዎድሮስ በለጠ እና በአጥናፉ ቡሽና ጎሎች 2-2 በሆነ አቻ ውጤት ጨዋታውን ማጠናቀቅ ችለዋል።
ውጤቱን ተከትሎ አዲስ አበባ ከተማ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ወደ 2019 የኢትዮጵያ ሊግ አንድ መውረዱን አረጋግጧል ።
10:00 ሰዓት ላይ ተጠባቂ የነበረው የደሴ ከተማ ከ ሀላባ ከተማ መካከል የተደረገው ጨዋታ በሀላባ ከተማ 1-0 አሸናፊነት ተጠናቋል።

በጨዋታው የሀላባ ከተማ እና የደሴ ከተማ ደጋፊዎችን ጨምሮ በርካታ የእግር ኳስ ተመልካቾች ሀዋሳ አርቴፊሻል ሜዳ ተገኝተው ጨዋታውን ተከታትለዋል።
በጨዋታው መጠናቀቂያ ደቂቃ እስራኤል ሸጎሌ ለሀላባ ከተማ ግብ አስቆጥሮ ጨዋታው በሀላባ ከተማ 1-0 አሸናፊነት ሲጠናቀቅ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ሀላባ ከተማ አንድ ቀሪ ጨዋታ እየቀረው ወደ 2019 ሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ማደጋቸውን አረጋግጠዋል ።
የሀላባ ከተማ አሰልጣኝ በሽር አብደላ በተከታታይ ለሁለተኛ ዓመት ሁለት ቡድኖችን ወደ ፕሪሜር ሊግ ማሳደግ የቻለ ሲሆን በ2017 ሸገር ከተማን እና በ2018 ሀላባ ከተማን ማሳደግ ችሏል።
ከጨዋታው መጠናቀቅ በኋላ በሽር አብደላ በሰጠው አስተያየት ሁሉም ነገር ከኔ ሳይሆን ከፈጣሪ ነው የሆነው ሊጉ ከባድ ቢሆንም በፈጣሪ እርዳታ ማሳካት ችለናል በማለት ተናግሯል።
20ኛ ሳምን ሁለተኛ ቀን ሶስት ጨዋታዎች ዛሬ የተደረጉ ሲሆን ላለመውለድ እየተደረገ የሚገኘው ጨዋታ አጓጊ ሆኗል።

4:00 ሰዓት ላይ የተደረገው ደብረ ብርሃን ከተማ ከ አድዋ ጨዋታቸውን አድርገው ያለ ግብ 0-0 በሆነ አቻ ውጤት ጨዋታቸውን አጠናቀዋል።
6:30 ሱሉልታ ክ/ከተማ ከንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ጋር ያደረገውን ጨዋታ 1-1 በሆነ አቻ ውጤት ሲጠናቀቅ በመጀመሪያ አጋማሽ 45ኛ ደቂቃ ላይ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ በተመስገን ኤርሚያስ ጎል ቀዳሚ በመሆን ወደ መልበሻ ክፍል አምርቷል።

ሁለተኛ አጋማሽ 67ኛ ደቂቃ ሱሉልታ ክ/ከተማ የሱሉልታ ክ/ከተማ አጥቂው ኪያ ወርቁ ግብ አስቆጥሮ ጨዋታው 1-1 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቋል።
የ20ኛ ሳምንት መጨረሻ ጨዋታ የነበረው አዲስ ከተማ ክ/ከተማ ከመንጌ ቤላሻንጉል ያደረጉት ጨዋታ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ 2-1 አሸናፊነት ተጠናቋል ።
በመጀመሪያ አጋማሽ ብርሃኑ ቶሎሳ 11ኛው ደቂቃ ላይ አዲስ ከተማ ክ/ከተማን መሪ ያደረገች ጎል ሲያስቆጥር በ17ኛው ደቂቃ ሲራጅ ከድር መንጌ ቤላሻንጉልን አቻ አድርጓል።

በ21ኛ ደቂቃ ላይ በድጋሚ ብርሃኑ ቶሎሳ ለአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ጎል አስቆጥሮ ጨዋታው ተጨማሪ ግብ ሳይቆጠር በዛው ውጤት 2-2 በአዲስ ከተማ አሸናፊነት ተጠናቋል።
ሲራጅ ከድር በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ 8 ግቦችን በማስቆጠር የከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ ደረጃ እየመራ ይገኛል።

