የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ከቡሩንዲ ጋር ለሚያደርገው የዓለም ዋንጫ ሁለተኛ ዙር ጨዋታ ያደረገውን ዝግጅት አስመልክቶ የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ !

የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ለዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ሁለተኛ ዙር ጨዋታ በነገው ዕለት በግንቦት 16 በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ታደርጋለች።

የምልመላ ህደት ጊዜ አጭር ስለነበረ በቡድን ግንባታ ላይ ትኩረት አድርገን ሰርተን ከፕሪምየር ሊግና ከከፍተኛ ሊግ የመለመልናቸው አዳዲስ የተካተቱ ተጨዋቾች አሉ እነሱን አብረን የቡድን ሥራ ላይ ትኩረት አድርገን አንድ የወዳጅነት ጨዋታ ነው ያገኘነው ጊዜው አጭር ስለሆነ ባለን ጊዜ አንድ ወዳጅነት ጨዋታ ከኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ ጋር አድርገን 4-0 አሸንፈናል ሜዳ ላይ እና ክፍል ውስጥ ክፍተቶቻችን ለመድፈን ሞክረናል የቡሩንዲ ጨዋታ ቪዲዮ ለማግኘት ሞክረናል የተወሰነ ሀይላይት ነገር አግኝተና ወደ 20 ደቂቃ በዛ ውስጥ ለመገምገም የተወሰነ ነገሮችን አይተናል ጠንካራ ትናንት ከነበረው ከደቡብ ሱዳን የተሻለ ጠንካራ ብሔራዊ እንደሆነ አይተናል በማለት አሰልጣኝ ራውዳ አሊ ገልፃለች።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን አንበል ምህረት ወሰኑ ከቡሩንዲ ጋር ለሚናደርገው ጨዋታ ዝግጅት በጣም አጭር ጊዜ ነበር ወሳኝ ጨዋታ ነው ቀድመን በሜዳችን ነው ቡሩንዲን የሚንገጥመው ጠንካራ ብሔራዊ ቡድን ነው እኛም የተሻለ ነገር አድርገን በሜዳችን ነው ኢትዮጵያ ህዝብ ከጎናችን ቢሆን ድጋፍ ብያደርግልን አሪፍ ነው ብዬ አስባለሁ ከፈጣሪ ጋር የተሻለ ነገር አድርገን ወደ ሶስተኛ ዙር እናልፋለን በማለት ተናግራለች።

የምልመላ ህደት ከባለፈው ለየት ባለ መልኩ ብዙ ውጣ ውረድ የነበረበት በባለፈው ምልመላ ውድድር ላይ ያልነበሩ ልጆችን አሳትፈናል ሁለተኛ ዙር ውድድሩ እየተጠናከረ ስለሚመጣ እነዛ ልጆች በተቻለ መጠን በፕሪሚየር ሊግ እና በከፍተኛ ሊግ ለመተካት ችለናል በማለት ራውዳ ዓሊ ገልፃለች።

በኢትዮጵያ በዕድሜ እርከን ላይ እየሰራን አይደለንም ሴቶች ላይ ከ17 ዓመት በታች ውድድር የለም  በጣም ብዙ ትግል ውስጥ ነው ያለነው ባልሰራንበት ነገር ላይ ውጤት ለማምጣት እየሰራን ነውና ከዚህ በኋላ ክለቦች ኃላፊነት መውሰድ አለባቸው ልክ እንደ ወንዶቹ ውድድር ግዴታ በክለብ ላይሰንሲንግ ከ17 ዓመት በታች ውድድር ከ20 ዓመት በታች ውድድር ሊያስገድዳቸው ይገባል በማለት ራውዳ ዓሊ ገልፃለች።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *