የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ ከማላዊ ጋር ብሔራዊ ቡድን ጋር በድሬዳዋ ስታዲየም ከሚያደርገው የወዳጅነት ጨዋታ አስመልክቶ ሀሳቡን ሰጥቷል።
5 ቀን ያህል ልምምድ አድርገናል የተመረጡ ልጆቹን ከጨዋታ የመጡ ስለሆኑ ትኩረት የሰጠነው በብዛት በታክቲክ እንድሁም የስነ ልቦና ዝግጅት ላይ ነው ያተኮርነው የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በሁለቱም ከተሞች ውድድሩን ተመልክተናል 23 ተጨዋቾችን ነው የመረጥነው ጥሩ ሆነው ግን ያልተመረጡ ተጨዋቾች ካሉ አራት ሳምንት ቀሪ የፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች አሉ ደግመን መመልከት እንችላለን ችግር የለብንም ሲል ዋና አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ ተናግሯል።
ስለ አዲስ ግደይ ጉዳት
አዲስ ግደይ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሲመጣ ሰባት ቀን አርፎ የመጣው 34ኛ ሳምንት ጨዋታ ላይ አልተሳተፈም የማዕዘን ምት (ኮርና) ሲመታ ነው የወደቀው ብቻውን ነው የተጎዳው በማለት ስለጉዳት ሁኔታ ገልጿል።
ሲለ መስፍን ታፈሰ
መስፍን ታፈሰ 34ኛ ሳምንት ጨዋታ ላይ በሚጫወትበት ወቅት ጉዳት ማስተናገዱን እንድሁም ተቀይሮ ሲወጣ ተከታትለናል ግን ራሱ ሆቴል ድረስ በመምጣት አመስግነው ለሀገር እንዳገለግል ስለመርጣችሁኝ ጉዳት ገጥሞኛል ይቅርታ ይደረግልኝ ብሎ ሆቴል ድረስ በመምጣት አነጋግሮናል በሰዓት እኔ አዳማ ስለነበርኩኝ ስልክ ደውሎ ሆቴል ድረስ መጥቼ ነበረ ይቅርታ ይደረግልኝ በዚህኛው ጉዳት ላይ ነኝ በማለቱ ምክንያቱም ያከበረው እኛን ሳይሆን ሀገሩን ነው እንደዚህ አይነት ተጨዋቾች ናቸው የሚያስፈልጉን ልከበር ይገባል በማለት ዮሐንስ ሳህሌ ገልጿል።
ስለ ብሔራዊ ቡድን ሲብስብ
መስፍን ታፈሰና አዲስ ግደይ በጉዳት ምክንያት ከሲብስቡ ሲወጡ 21 ልጆች አሉ ከ21 ልጆች መካከል 50% በላይ ወይም 11 ልጆች አዲስ ጥሪ የተደረገላቸው ናቸው 10 ልጆች ባለፈው ከሳውቶሜ እና ፒሪንሲፔ ጋር በነበረው ጨዋታ የነበሩ ናቸው 50% ዕድል ሰጥተናል ሲል ገልጿል።
አሁን ከተያዙ ልጆች 80% ብሔራዊ ቡድን የሚሆኑት እነዝህ ናቸው ቀሪዎች ጋቶች ፓኖም ፣ ከነዓን ማርክነህ እና አቤል ያለው ይጨመራሉ በመሀል የሚጨመሩ ልጆችም ልኖሩ ይችላሉ ከዛ ባሻገር ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ላይ ፌዴሬሽኑ ጊዜ ከሰጠን ጫና ሳንፈጥርባቸው ወደፊት ብሔራዊ ቡድኑን የሚተኩ ልጆች መጥተው አብሮ እንዲሰሩ እናደርጋለን በማለት ሀሳቡን ሰጥቷል።
ስለ ሚዲያ
የግል ጥላቻ ምናምን ከሆነ አላውቅም እኔ ሚዲያ የመከልከል ስልጣን የለኝም የግልም ጥቅም የለኝ ከሚዲያ ጋር ተነካክቼም አላውቅም ነገር ግን ከሚዲያ ጋር ቅርበት አለኝ ሀገራዊ በሆነ ምክንያት ፍትሃዊ በሆነ መንገድ ነው የመጀመሪያ ጊዜ ብሔራዊ ቡድን ሲመጣ እኔ ነኝ ( Press Conference) ያስጀመርኩት ነገር ግን ፌዴሬሽኑ ነው ዌብሳይቱ ላይ ያስቀመጠው የነገው ልምምድ በዝግ ነው በማለት እኔ አላስቀመጥኩም ጋዜጠኞች ወደ ልምምድ ሜዳ እንዳይመጡ እኔ አልከለከልኩም ሲል ተናግሯል።
በጉዳት ምክንያት በወጡ ልጆች ምትክ ለምን አዳዲስ ተጨዋቾች አልተጨመሩም ?
አሁን ያሉ ልጆች 80% እነዝህ ልጆች ናቸው ብሔራ ቡድን የሚሆኑት ስለዝህ ሁሉም ሰርቶ ጥሪት አድርገን ማየት እንድንችል ነው 40 ሰው ጠርተን በግልፅ እያንዳንዱን ሰው ማየት አንችልም አራት ቀን ልምምድ ስንሰራ ሙሉ ልጆችን ሙሉ ሜዳ ተጠቅምን በምንፈልጋቸው ቦታዎች ላይ አሰልፈን ማየት ችለናል አሁንም 21 ተጨዋቾች አሉን ሁሉም ይጫወታሉ እኛ ሙከራ አይደለም የያዝነው ብሔራዊ ቡድኑ ላይ ሊቆይ የሚችል ሰው ፍለጋ ላይ ነን ያለው ቁጥር ያላበዛው ዕድል ለመስጠት ሲል አሰልጣኝ አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ ገልጿል።
