የለሚ ኩራ ክ/ከተማ ሴቶች እግር ኳስ ክለብ የቅሬታ ደብዳቤ ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አቀረበ!

የለሚ ኩራ ክ/ከተማ ሴቶች እግር ኳስ ክለብ የቅሬታ ደብዳቤ ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አቀረበ!

የኢትዮጵያ ሴቶች ከፍተኛ ሊግ የ2018 ዓ.ም ውድድር በሰበታ ክ/ከተማ መጠናቀቁ የሚታወስ ሲሆን የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ሴቶች እግር ኳስ ክለብ በ2018 ዓ.ም የኢትዮጵያ ሴቶች ከፍተኛ ተሳታፊ በመሆን ውድድሩን 4ኛ ደረጃ በመያዝ ያጠናቀቀ ቢሆንም ግን ከውድድሩ ደንብና መመሪያ ውጪ በሆነ መልኩ 3ኛ ደረጃ ሆነን ማጠናቀቅ ሲገባን ደረጃችንን ተነጥቀናል ሲሉ ቅሬታቸውን ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በደብዳቤ አቅርበዋል።

የ2018 ዓ.ም የፕሪሚየር ሊጉ እና የከፍተኛ ሊግ ሴት ክለቦች የውድድር ደንብ ምዕራፍ 7 አንቀፅ 1 ንዑስ አንቀፅ 6 ላይ እንደተገለፀው ከተራ ቁጥር 1 እስከ 5 በተጠቀሱት እኩል ከሆኑ ክለቦች በሁለቱም ዙር እርስ በርሳቸው ሲጫወቱ የተሻለው ውጤት ያስመዘገበ ክለብ ሻምፕዮን ይሆናል ይላል።

በዚህም መሠረት በመጀመሪያ ዙር
በሀዋሳ አርቴፊሻል ስታዲየም

ፋሲል ከነማ 1-4 ለሚ ኩራ ክ/ከተማ

የሁለተኛ ዙር ጨዋታ በሰበታ ስታዲየም

ለሚ ኩራ ክ/ከተማ 0-1 ፋሲል ከነማ

በዝህም በደርሶ መልስ ለሚ ኩራ 4-2 ፋሲል ከነማ በማሸነፍ የተሻለው ውጤት አስመዘግበናል ሲሉ ቅሬታቸውን አቅርበዋል።

የውድድር ውጤት ነጥብ አሰጣጥ ምን ይላል

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *