በተጠናቀቀው የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ ጠንካራ ተፎካካሪ በመሆን ሁለተኛ ደረጃ ይዞ ማጠናቀቅ የቻለው ኢትዮ ኤሌክትሪክ የዋና አሰልጣኝ ውል ለተጨማሪ ዓመት ሲያራዝም ክለቡን በለቀቁ ተጨዋች ምትክ አዳዲስ ተጨዋቾችን ወደ ሲብስቡ ለመቀላቀል ከስምምነት ላይ ደርሷል።

ዋና አሰልጣኝ ኤርሚያስ ዱባለ ኢትዮ ኤሌክትሪክን በመረከብ ጠንካራ ተፎካካሪ ማድረግ የቻለ ሲሆን ለቀጣይ ሁለት ዓመታት በክለቡ ለመቆየት ከስምምነት ላይ ደርሷል።

ቤተልሄም መንተሎ ከመቻል ፣ ሒሩት ተስፋዬ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፣ ሲሳይ ገ/ዋህድ ከመቻል ፣ ታሪኳ ጴጥሮስ ከሀዋሳ ከተማ ፣ ሚለን ጋይም ከቦሌ ክ/ከተማ ፣ መሠረት ወርቅነህ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፣ አበባየሁ ጣሰው ከመቻል ፣ መቲ ረታ እና ረድኤት ክንዴ ከልደታ ክ/ከተማ አዲስ ቡድኑን ለመቀላቀል ስምምነት ላይ የደረሱ ተጨዋቾች ሲሆን ፀጋነሽ ዎራና ፣ ትዕግስት ያዴታ ፣ ንዕግስቲ መዓዛ ፣ ቤተልሄም በቀለ ፣ ባንቺይርጋ ተስፋዬ ፣ ገብርኤላ አበበ ፣ ብርሃን ኃ/ሥላሴ ፣ ህዳዓት ካሱ እና እየሩሳለም ወንድሙ በኢትዮ ኤሌክትሪክ ለመቆየት ውላቸውን ያራዘሙ ተጨዋቾች ሆነዋል።



