መቻል ሁለት አዳዲስ ተጨዋቾችን ሲያስፈርም የአራት ነባር ተጨዋቾች ውል አድሷል !

መቻል ሁለት አዲስ ተጫዋቾችን ሲያስፈረም የነባር ተጨዋቾች ውል ለማደስ ከስምምነት ላይ ደርሷል።

በ2018 የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ ሶስተኛ ደረጃ ይዞ በማጠናቀቅ የነሃስ ሜዳሊያ አሸናፊ መሆን የቻለው የመቻል ሴት እግር ኳስ ቡድን የአራት ተጫዋቾችን ውል ሲያራዝም ሁለት ተጫዋቾችን ወደ ስብስቡ ቀላቅሏል።

ያለፉት ዓመታት በሀዋሳ ከተማ ጥሩ ጊዜ ማሳለፍ የቻለችው ሁለገብ ተጨዋች ፀሐይነሽ ጁላ እና በኢትዮ ኤሌክትራክ የተከላካይ አማካይ ድንቅ ጊዜ ያሳለፈችው ዙፋን ደፈርሻ መቻልን የተቀላቀሉ አዳዲስ ተጨዋቾች ሲሆኑ የግራ መስመር ተከላካይ ነፃነት ፀጋዬ ፣ የተከላካይ አማካይ ፂዮን ፈየራ ፣ አማካይ ቱፊት ካዲዮ እና የአጥቂ ስፍራ ተጫዋቿ ትግስት ወርቄ ለቀጣይ ሁለት አመት በመቻል ቤት ለመቆየት ከስምምነት ላይ ደርሰዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *