ዲሲ ዩናይትድ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ጋር ሊያደርጉት የነበረው የወዳጅነት ጨዋታ ተሰርዟል !

ዲሲ ዩናይትድ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ጋር ሊያደርጉት የነበረው የወዳጅነት ጨዋታ በቪዛ እና በቅርቡ በተከሰተው የኢቦላ ወረርሽኝ በሽታ ዙሪያ በተወሰዱ እርምጃዎች ምክንያት መሰረዙን ዲስ ዩናይትድ አስታውቋል።

በኦዲ ፊልድ ስታዲየም ሊደረግ የነበረው ጨዋታ እንደማይካሄድ ተረጋግጧል።

ለጨዋታው የተሸጡ ቲኬቶችን በቀጥታ ከክለቡ ወይም በቲኬት ማስተር የገዙ ደጋፊዎች በግዢ ወቅት ጥቅም ላይ የዋለውን የመጀመሪያውን የክፍያ ዘዴ ሙሉ በሙሉ ተመላሽ እንደሚሆን ክለቡ ገልጿል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *