ወደ 2019 ሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ለማደግ ከጋሞ ጨንቻ ጋር እየተፎካከረ የሚገኘው የካ ክ/ከተማ ወሳኝ ድል አስመዝግቧል።

የካ ክ/ከተማ ከንብ ጋር ያደረገውን ጨዋታ በወለላ ሸምሱ ብቸኛ ግብ 1ለ0 በማሸነፍ ወደ ሀገራችን ትልቁ ሊግ ለመግባት በሚያደርገው ፉክክር ውስጥ እራሱን ማቆየት ችሏል።
በጋሞ ጨንቻ እና የካ ክፍለ ከተማ መካከል ያለው የነጥብ ልዩነት በድጋሚ ወደ 2 መጥበብ ችሏል።
ቀጣይ የመጨረሻ 18ኛ ሳምንት
ጋሞ ጨንቻ ከ ቡራዩ ክ/ከተማ
የካ ክ/ከተማ ከባቱ ከተማ
ባቱ ከተማ በሰፊ የጎል ልዩነት ቡራዩ ክ/ከተማን አሸንፏል።
ያለፉትን ሁለት ጨዋታዎች በቤንች ማጂ ቡና እና ንብ ሽንፈት አስተናግዶ የነበረውና ባቱ ከተማ ቡራዩ ክ/ከተማን 5ለ1 ማሸነፍ ችሏል
የባቱ ከተማ ማሸነፊያ ግቦችን በ3ኛ ደቂቃ ይሁን መልካሙ በ43ኛ ደቂቃ አብርሃም አልዲ 45ኛ ደቂቃ ምስጋናው አንጋሳ በማስቆጠር የመጀመሪያ አጋማሽ 3ለ0 መሪነት ወደ መልበሻ ክፍል ያመሩ ሲሆን በሁለተኛ አጋማሽ 67ኛ ደቂቃ ተማም ከድር በጭማሪ ደቂቃ 90+2 ዳዊት ታደለ አስቆጥሮ 5ለ1 ጨዋታው ልጠናቀቅ ችሏል።
የቡራዩ ክፍለ ከተማ ብቸኛዋን ግብ 90ኛ ደቂቃ ናኩማር በቀለ አስቆጥሯል።
ዳዊት ታደለ ጎል ማስቆጠሩን ተከትሎ ያስቆጠራቸውን የጎል መጠን ወደ 5 ከፍ በማድረግ ኮከብ ጎል አስቆጣሪዎች ዝርዝር ውስጥ መግባት ችሏል።

