የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ 17ኛ ሳምንት ምድብ ለ ሀዋሳ አርቴፊሻል ስታዲየም ዛሬ ሁለተኛ ቀን ሁለት ጨዋታዎች የተከናወነ ሲሆን 7:30 ደብረ ብርሃን ከተማ 1ለ0 ቦዲቲ ከተማን ማሸነፍ ችሏል።
በጨዋታው ደብረ ብርሃን ከተማዎች 13ኛው ደቂቃ አካባቢ ከማዕዘን ምት የተሻገረውን ኳስ የቦዲቲ የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች የሆነው አባተ ዓለሙ ከራሱ የሜዳ ክልል ለማራቅ አክሪሮ በሚመታበት ወቅት ከፊቱ በነበረው ሌላኛው የቦዲቲ ከተማ ተከላካይ አስጨናቂ ደራ ላይ አልፎ ጎል ልሆን ችሏል።

ጨዋታውም ተጨማሪ ጎል ሳይቆጠር በዛው ውጤት የተጠናቀቀ ሲሆን ደብረ ብርሃን ከተማ ከነበረበት 9ኛ ደረጃ አንድ ደረጃ በማሻሻል ከንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ የግብ ክፊያ ተሽሎ በእኩል 17 ነጥብ ከወራጅ ቀጠና መውጣት ችሏል።
ቦዲቲ ከተማ 15 ጨዋታዎች አድርጎ 14 ነጥቦችን በመሰብሰብ 10ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል
የቀኑ ሁለተኛ ጨዋታ 10፡00 ላይ የተካሄደ ሲሆን አዲስ ከተማ ክ/ከተማ 2ለ0 ሱሉልታ ክፍለ ከተማን አሸንፏል።
በመጀመሪያ አጋማሽ 20ኛ ደቂቃ ላይ የሱሉልታ ተከላካይ ጋትኩት የሰራውን ስህተት የተጠቀሙት አዲስ ከተማ ክ/ከተማዎች ፋሲካ መስፍን ወደ ጎል ለመምታት በሚሞክሩበት ወቅት የተቆረጠ የሚመስል ኳስ ያብቃል ፈረጃ ጋር ደርሶ ያብቃል ፈረጃ ጎል አስቆጥሮ የመጀመሪያ አጋማሽ መጠናቀቅ ችሏል።

ሁለተኛው ጋማሽ 50ኛ ደቂቃ ላይ ፋሲካ መስፍን ከተከላካይ ጀርባ የተጣለውን ኳስ ቀድሞ አሸንፎ ከዛም ለ አማካዩ ግሩም አለማየሁ ወደኋላ የቀነሰውን ኳስ ግሩም አለማየሁ በግሩም ሁኔታ ወደ ግብነት ቀይሮ ጨዋታው 2ለ0 በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ አሸናፊነት መጠናቀቅ ችሏል።

አዲስ ከተማ ክ/ከተማ 15 ጨዋታ አድርጎ 22 ነጥቦችን በመሰብሰብ 5ኛ ደረጃ ላይ ሲገኝ ሱሉልታ ክ/ከተማ 16 ጨዋታዎችን አድርጎ በተመሳሳይ 22 ነጥቦችን በመሰብሰብ 6ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

ቀጣይ ጨዋታ መርሐ-ግብር 18ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር እሁድ መጋቢት 27/2018 እና ሰኞ መጋቢት 28/2018 ቀጥሎ ይካሄዳል

