የኢትዮጵያ ክፍተኛ ሊግ ምድብ ለ 17ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ዛሬ በሀዋሳ አርቴፊሻል ስታዲየም መካሄድ ጀምሯል!
4:00 ሰዓት ላይ በአሰልጣኝ መሐመድ ኑር የሚመራው መንጌ ቤላሻንጉል ከክፍሌ ቦልተናው አዲስ አበባ ከተማ ጋር ያደረጉት ጨዋታ የ17ኛ ሳምንት ምድብ ለ ቀዳሚ ጨዋታ ሲሆን በመንጌ ቤላሻንጉል 1ለ0 አሸናፊነት ፍጻሜውን አግኝቷል።
በ79ኛው ደቂቃ አካባቢ የአዲስ አበባ ከተማ ግብ ጠባቂ ሌሊሳ ኦላና በሰራው ጥፋት የፍፁም ቅጣት ምት ማግኘት የቻሉት መንጌ ቤላሻንጉሎች የተገኘውን የፍፁም ቅጣት ምት የኋሸት ሰለሞን ጎል አስቀጥሮ 1ለ0 ማሸነፍ ችለዋል።
ደረጃቸውን ማሻሻል ባይችሉም ነጥባቸውን ግን ከፍ አድርገው በ16 ጨዋታዎች 25 ነጥቦችን በመሰብሰብ 3ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።
አዲስ አበባ ከተማ ሽንፈት ማስተናገዱን ተከትሎ በነበረበት 8 ነጥቦችን በመሰብሰብ 11ኛ ደረጃ ላይ ለመቆየት ተገዷል።

ቀን 7:30 በተደረገው በአሰልጣኝ ደጃም የሚመራው ቢሾፍቱ ከተማ በአሰልጣኝ ዘላለም ሽፈራው የሚመራው ደሴ ከተማ ጨዋታ አድርገው 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቋል።
በጨዋታው ቀድሞ ጎል ማስቆጠር የቻሉት ቢሾፍቱ ከተማዎች ሲሆን ከመዓዘን ምት ሽመልስ ቦጋለ ያሻማውን ኳስ ኤፍሬም ገረመው በግንባሩ ገጭቶ 63ኛው ደቂቃ ላይ ቢሾፍቱ ከተማን መሪ ማድረግ ብችልም በ69ኛ ደቂቃ ሲሳይ ከደሴ ከተማ በኩል በቀይ ካርድ ከሜዳ በመውጣቱ የቁጥር ቢልጫ ያገኙት ቢሾፍቱ ከተማዎች ብዙም ሳይቆይ በ73 ደቂቃ ከቅጣት ምት ግብ ጠባቂው እንዳሻው እሸቴ ያሻማውን ኳስ በቀይ ቢላል ገመዳ አስቆጥሮ ጨዋታው 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት መጠናቀቅ ችሏል።

10:30 ሰዓት ላይ በተካሄደው ጨዋታ በወጣቱ አሰልጣኝ በሽር አብደላ የሚመራው መሪው ሀላባ ከተማ ከእዝሮን ስዩም ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ጋር ያደረገውን ጨዋታ በሰፊ የጎል ልዩነት ሀላባ ከተማ ማሸነፍ ችሏል።
ሀላባ ከተማ 16ኛ ደቂቃ ላይ ፀጋ ደርቤ ከ ታምራት በቀለ በግራ መስመር አንድ ሁለት ተቀባብለው ሳጥን ውስጥ ከገቡ በኋላ ሰለሞን ገመቹ ለዮናታን ኋይሉ ሲያቀብ ከጀርባ ሙሉጌታ ካሳሁን መኖሩን አይቶ የተወለትን ኳስ ሙሉጌታ ካሳሁን እድሉን በአግባቡ ተጠቅሞ ጎል በማስቆጠር ሀላባ ከተማ የመጀመሪያው ጎል ማስቆጠር ችሏል።
የመጀመሪያ አጋማሽ ልጠናቀቅ አንድ ደቂቃ ሲቀረው ኪሩቤል ፍቅረማርቆስ ከራሱ የሜዳ ክፍል ያሻማው የቅጣት ምት ተጨራርፎ ዮናታን ኋይሉ ከደረሰ በኋላ ሙሉጌታ ካሳሁን ወደኋላ ለሰለሞን ገመቹ የሰጠውን ኳስ ሰለሞን ገመቹ በጥሩ ሁኔታ ለያሬድ መሐመድ አቀብሎ ያሬድ መሐመድ በጥሩ አጨራረስ ሁለተኛ ጎል አስቆጥሮ ለእረፍት 2ለ0 ሀላባ ከተማ እየመራ ወደ መልበሻ ክፍል ማምራት ችሏል።
ከረፍት እንደተመለሱ 52ኛው ደቂቃ ላይ ከማዕዘን ምት ምስክር መለሰ ያሻማውን ኳስ ኪሩቤል ፍቅረ ማርቆስ ጎል አስቆጥሮ ሀላባ ከተማ 3ለ0 እንድመራ ያስቻለውን ጎል ማስቆጠር ሲችል ጅላሉ ሙህዲን ያሸነፈውን የአየር ላይ ኳስ 71ኛው ደቂቃ ላይ እስራኤል ሻጎ ከመሃል መዳ ድሬስ በቀኝ መስመር እየገፋ ወስዶ 4ኛውን ጎል በራሱ ጥረት ማስቆጠር ችሏል።
በፀጋ ደርቤ አማክኝነት የፍፁም ቅጣት ምት ሀላባ ከተማ አግኝቶ ዮናታን ኃይሉ ጎል አስቆጥሮ ጨዋታውን ሀላባ ከተማ 5ለ0 ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ አሸናፊነት ተጠናቋል።

የ17ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ምድብ ለ ጨዋታዎች መጋቢት 24 በነገው ዕለትም ቀጥሎ የሚካሄድ ይሆናል
7:30 ቦዲቲ ከተማ ከ ደብረብርሃን ከተማ
10:30 ሱሉልታ ክ/ከተማ ከ አዲስ ከተማ ክ/ከተማ የሚጫወቱ ይሆናል።

የደረጃ ሰንጠረዡን ሀላባ ከተማ ከተከታዩ ደሴ ከተማ በአራት ነጥቦች በመብለጥ በ34 ነጥብ 1ኛ ደረጃ ላይ የሚገኙ ቡድን ሲሆን ንፋስ ስልክ ላፍቶ 17 ነጥቦችን በመሰብሰብ 8ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

