የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር ከገጠመውን የፋይናንስ ችግር ለማስታገስ የሚያስችል የ100 ሚሊየን ብር ድጋፍ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፥ ከሚድሮክ ግሩፕ እና ከቢ ጂ አይ ኢትዮጵያ አግኝቷል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት ዛሬ በተካሄደ መርሐ ግብር ላይ
ቅዱስ ጊዮርጊስ የእግርኳስ ክለብ የተጫዋቹ እና የማህበሩ ብቻ ሳይሆን አንዱ የከተማችን ጠንካራ ክለብ ነው ያሉት ክብርት ከንቲባ በመሆኑም ይህንን የሀገራችንን እና ከተማችንን የወከለውን ታሪካዊ ክለብ ከመፍረስ የመታደግ ኃላፊነት እንዳለብን እናምናለን ይህ አንጋፋው ክለብ ላለፋት 6 ወራት ደመወዝ መክፈል በማይችልበት ደረጃ ላይ ደርሶ እና የመበተን አደጋ ተጋርጦበት ማየት ስለሌብን ከከተማችን በጀትም ወስነን፣ ለባለሀብቶች ባቀረብነው ጥያቄ መሰረት ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ እና ቢጂአይ ኢትዮጵያ በሰጡን ፈጣን ምላሽ በጥቅሉ የ100 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ለተቋቋመው ጊዜያዊ ኮሚቴ አስረክበናል ብለዋል።
👉ሚድሮክ ግሩፕ 50 ሚሊዮን
👉ቢ.ጂ.አይ ኢትዮጵያ 40 ሚሊየን ብር
👉የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር
10 ሚሊየን ድጋፍ አድርገዋል፡፡
የ50 ሚሊየን ብር ድጋፍ ያደረገው አንጋፋው የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር ታሪካዊ አጋር የሚድሮክ ግሩፕ ስራ አስፈጻሚ አቶ ጀማል አህመድ በበኩላቸው ድርጅታቸው በቀረበለት ጥያቄ መሰረት ለታሪካዊ አጋሩ ቅዱስ ጊዮርጊስ ድጋፍ በማድረጉ ደስተኛ መሆናቸውን ገልፀው ወደፊትም ክለቡ በተቋማዊነት ጎዳና እንዲጓዝ ሁሉም አካል ድርሻውን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ኢትዮጵያ የእግር ኳስ ታሪክ ውስጥ ገናና ስም ያለውና በ1928 ዓም የተመሰረተው በያዝነው ዓመት 90 ዓመት የሞላው ቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ክለብን ወደ ቀደመ ዝናው ለመመለስ ሚድሮክ የበኩሉን ድርሻ ይወጣል ሲሉ አቶ ጀማል አህመድ ገልፀዋል።
ሌላኛው አጋር ቢ.ጂ.አይ ኢትዮጵያ የማርኬቲንግ ሀላፊ አቶ አብዱልቃድር ማማ ባደረጉት ንግግር ቢ.ጂ.አይ ኢትዮጵያ ቅዱስ ጊዮርጊስን እንዲያግዝ በመጠራቱ ታላቅ ደስታ ይሰማዋል ብለዋል፡፡
