19ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ (ሲቲ ካፕ) “ህዳሴ ዋንጫ” በሚል ስያሜ እሁድ ይጀመራል።

ዛሬ በተከናወነው የዕጣ ማውጣት ስነ-ስርዓት

በምድብ “ሀ”
👉ቅዱስ ጊዮርጊስ
👉ፋሲል ከነማ
👉አዳማ ከተማ
👉መቻል

በምድብ “ለ” 
👉ኢትዮጵያ ቡና
👉ኢትዮ. ኤሌክትሪክ
👉ሸገር ከተማ
👉ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

የታላቁ ህዳሴ ግድብ መጠናቀቅን ተከትሎ “ህዳሴ ዋንጫ” የሚል ስያሜ የተሰጠው ውድድር የፊታችን እሁድ በአዲስ አበባ ስታዲየም መከናወን ይጀምራል።

የመክፈቻ ጨዋታ

እሁድ መስከረም 18/2018

⌚️8:00 ሰዓት
ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ መቻል

⌚️ 10:00 ሰዓት
ፋሲል ከነማ ከ አዳማ ከተማ

ተመልካቾች ወደ ስታዲየም ገብተው እንዲታደሙ እየተሰራ እንደሆነም በመግለጫው ተነስቷል።