በኢትዮጵያ ሊግ አንድ ምድብ ሀ ተደልድሎ ውድድሩን እያካሄደ የሚገኘው ይርጋጨፌ ቡና እግር ኳስ ክለብ ለሁለተኛው ዙር ዝግጅታቸውን ከወድሁ በመጀመር ወደ 2019 የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ለማደግ ቆርጠው መንሳታቸውን ገልፀዋል።
ከዝህ ቀደም በሰንዳፋ በኬ ፣ በሞጆ ከተማ ፣ በለገጣፎ ለገዳዲ ፣ በባቱ ከተማ ፣ በመልካ ኖኖ ክ/ከተማ ፣ በጅማ አባ ቡና እና ሰበታ ማሰልጠነ የቻለው ዋና አሰልጣኝ ኢዮብ ዋቤ (ሊፒ) የሚመራው ይርጋጨፌ ቡና እግር ኳስ ክለብ ዋናው አላማቸው ወደ 2017 የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ማደግ እንደሆነ ገልፀዋል።

የክለቡ ሥራ አስኪያጅ አሰጋኸኝ ጉዬ በበኩላቸው እንደተናገሩት የዞኑ መንግስት ለክለቡ በሰጠው ልዩ ትኩረት የጌዲኦ ዞን የበላይ አመራሮች ያመሰገኑ ሲሆን ክለቡን ወደ ከፍተኛ ሊግ ለመመለስ ከወድሁ የቤት ሥራዎችን እየሰሩ እንደሚገኙ ገልፀዋል።
እሁድ ጥር 10/2017 ተስተካካይ ጨዋታ ወልቂጤ ከተማ ከ ይርጋጨፌ ቡና ይጫወታል።

