የ2018 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር

1.ጥቅል መረጃዎች
⚽️ በውድድሩ 20 ክለቦችን ይሳተፋሉ::
⚽️ 380 ጨዋታዎች ይደረጋሉ።
⚽️ ውድድሩም 10 ክለቦችን በያዙ  ሁለት ምድቦች (ምድብ 1 እና ምድብ 2) ተከፍሎ በሁለት ከተሞች  በ2 ዙር ለ38 የውድድር ሳምንታት  ይካሄዳል።
⚽️ ሁሉም ክለቦች እርስ በእርሳቸው እንዲጫወቱ ለማድረግ  በአንድ ዙር ውስጥ ምድቦቹ ለ3 ጊዜ ያክል በአዲስ መልክ ይዋቀራሉ።
⚽️ ምድቦቹም የሚዋቀሩት ምድብ 1 የነበሩትን  5 ክለቦች ምድብ 2 ከነበሩት  5 ክለቦች ጋር በማቀያየር ይሆናል።

  1. የሳምንት ጨዋታዎች
    ⚽️ አንድ የውድድር ሳምንት 5 ቀናቶች ይኖሩታል ።
    ⚽️ በየምድቡ በእያንዳንዱ ሳምንት 5 ጨዋታዎች ይደረጋሉ።
    ⚽️ 5ቱ ጨዋታዎች በሁለት ቀን ከተደረጉ ሶሶት የእረፍት ቀናት እንዲሁም በሶስት ቀን ከተደረጉ ሁለት የእረፍት ቀን ይኖራል።
  2. የመርሃ ግብር ዝግጅት(መርሃ ግብሩ ክለቦች በወጣላቸው እጣ ቅደም ተከተል  የሚከተሉትን ታሳቢ በማድረግ ይዘጋጃል)
    ⚽️ አንድ ክለብ በተከታታይ ሁለት ጨዋታዎችን የሚጫወትበትን ዝቅተኛ የማገገሚያ  ጊዜ (ሁለቱ ጨዋታዎች የሚጀምርበት የሰዓት ልዩነት) የ72 ሰዓት
    ⚽️ ሁሉም ክለቦች የሚጫወቱበት ስታድየምና ሰዓት በማመጣጠን
    ⚽️ የደርቢ ጨዋታዎችን
    ⚽️ የብሮድካስት አጋር  ፍላጎትን
  3. መርሃ ግብሩ እንዲስተካክል የሚያደርጉ ሁኔታዎች(በውድድር ደንቡ ላይ የተቀመጠው እንደተጠበቀ ሆኖ)
    ⚽️ ውድድሩ የሚካሄድበት ስታድየሞች ሲታወቁ ክለቦች የሚጫወቱበት ቅደም ተከተል እንዲሁም የጨዋታ ቀንና ሰዓት ላይ የደርቢ ጨዋታዎችን መሰረት ባደረገ መልኩ ይስተካከላል።
    ⚽️ በአፍሪካ የክለቦች  እና በኢትዮጵያ ዋንጫ ውድድር  ላይ ተሳታፊ በሆኑት ክለቦች  ምክኒያት የውድድር ቀንና ሰዓት ላይ ለውጥ ሊደረግበት ይችላል፣
    ⚽️ የተመረጡ ጨዋታዎች ከምድቡ ሜዳ ውጪ በተለየ ሜዳ ሊደረጉ ይችላሉ

የመጀመሪያ ዘጠኝ ሳምንት ምድቦች

ምድብ አንድ
ወልዋሎ አዲግራት ዮኒቨርስቲ
ፋሲል ከነማ
ስሁል ሽረ
መቻል
ድሬደዋ ከተማ
ወላይታ ድቻ
ሀዋሳ ከተማ
መቐለለ 70 እንድርታ
ሲዳማ ቡና
ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

ምድብ ሁለት
ነገሌ አርሲ
ኢትዮጵያ ቡና
ኢትዮ ኤሌክትሪክ
ባህርዳር ከተማ
አዳማ ከተማ
ሸገር ከተማ
ኢትዮጵያ መድን
ሀድያ ሆሳዕና
አርባምንጭ ከተማ
ቅዱስ ጊዮርጊስ