የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ የ2018 የውድድር ዘመን ከመጀመሩ አስቀድሞ ከክለቦች ጋር ዛሬ በካሌብ ሆቴል በተደረገው ውይይት ከዚህ ቀደም በነረው የደሞዝ ጣርያ ዙርያ ውሳኔ ተላልፏል።

የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ የ2018 የውድድር ዘመን ከመጀመሩ አስቀድሞ ከክለቦች ጋር ዛሬ በካሌብ ሆቴል በተደረገው ውይይት ከዚህ ቀደም በነረው የደሞዝ ጣርያ ዙርያ ውሳኔ ተላልፏል።

በዛሬው የውይይት መድረክ ላይ ከዚህ ቀደም ተቀምጦ የነበረው ከፍተኛው 20,000 ብር የተጫዋች ደሞዝ ጣርያ ላይ ማስተካከያ እንዲደረግ ከተሳታፊዎች አስተያየት የተሰጠ ሲሆን ክቡር ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ የግለሰብ ደሞዝ ላይ ገደብ ማስቀመጥ ህግን የተከተለ አለመሆኑን በማንሳት ክለቦች ዓመታዊ የደሞዝ ጥቅል ጣርያ ማስቀመጥ እንደሚገባ ገልጸዋል።

በመጨረሻም ከዚህ ቀደም ተቀምጦ የነበረው የተጫዋቾች የደሞዝ ጣርያ እንዲነሳ በማድረግ ዓመታዊ 12 ሚልየን ብር የተጫዋቾች እና የቡድን አባላት ጥቅል የደሞዝ የበጀት ጣሪያ እንዲሆን በአብላጫ ድምጽ ተወስኗል።

ከዚህ ጥቅል ደሞዝ ጋር በተያያዘ ዝቅተኛ የተጫዋች ደሞዝ የሀገራችን ህግ ላይ በተቀመጠው ዝቅተኛ የደሞዝ እርከን መሠረት እንዲሆን ውሳኔ የተላለፈ ሲሆን ዝርዝር አፈጻጸሙም በቀጣይ ለክለቦች እንደሚገለጽ ከመድረኩ ተገልጿል።