የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ምድብ ለ 19ኛ ሳምንት የመጀመሪያ ቀን ውሎ !

ሀላባ ከተማ ከ ሶሎዳ አድዋ አቻ ተለያይቷል!

የኢትዮጵያ የከፍተኛ ሊግ ምድብ ምደብ ለ 19ኛ ሳምንት የመጀመሪያ ጨዋታ ሀላባ ከተማ ከሶሎድ አድዋ ያለ ጎል 0ለ0 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይተዋል።

በወጣቱ አሰልጣኝ በሽር አብደላ የሚመሩት ሀላባ ከተማዎች ወደ 2019 ሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ለማደግ ብርቱ ፉክክር እያደረጉ የሚገኙ ሲሆን በጨዋታ የፍፁም ቅጣት ምት ሁለተኛ አጋማሽ ላይ አግኘተው ማስቆጠር ሳይችሉ ቀርተዋል።

ሀላባ ከተማ በ35 ነጥቦች ምድቡን በመምራት ላይ የሚገኝ ሲሆን ከደሴ ከተማ ጋር ያለው የነጥብ ልዩነት ደሴ ከተማ እስክጫወት ወደ 4 ነጥብ ሰፍቷል።

በዋና ስልጣኝ አታክልቲ በርሄ የሚመራው ሶሎዳ አድዋ በዘንድሮ የውድድር ዓመት ከመውረድ ስጋት ለመራቅ እየተፋለመ የሚገኝ ሲሆን ከጨዋታው አንድ ውድ ነጥብ ማሳካት ችሏል።

በተከታይይ ከመሪዎች ሀላባ ከተማ እና ደሴ ከተማ ጋር ጨዋታው አድርጎ ሽንፈት ያላስተናገው ሶሎዳ አድዋ 19 ነጥቦችን በመሰብሰብ በጊዜያዊ የደረጃ ሰንጠረዥ 7ኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችሏል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *