የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ እኛ የሚያጠቁ ሰዎችን ነው በብዛት የቀየርነው ለማጥቃት ነው እንጅ ለመከላከል አይደለም እነሱ በመከላከሉ የተሻሉ ነበሩ በመጀመሪያ ጨዋታ ሁለተኛ አጋማሽ እነሱ ብልጫ ወስደው ነበሩ ዛሬ ደግሞ እኛ ነን ሁለተኛ አጋማሽ ብልጫ የወስድነው በአንድ ጊዜ ሁሉንም ነገር መሥራት የምንችል ብንሆን ካለንበት ደረጃ ከፍ ማለት እንችል ነበር እኛ የሚናየው እያደግን ነው ወይ እያሻሻልን ነው የሚለውን ነው የሚናየው ምክንያቱም በብዛት አዳዲስ ተጨዋቾችን ነው ቡድኑ ውስጥ ያካተትነው 11 አዳዲስ ተጨዋቾችን ነው የጨመርነው አዲስ ቡድን እየገነባን ነው ሲል ዮሐንስ ሳህሌ ተናግሯል።
ለውጦች አሉ በባለፈው ሳምንት እነሱ ነበሩ ጨዋታውን ተቆጣጥረው ሲጫወቱ ነበሩ በዛሬ ጨዋታ ግን ሳናፈገፍግ ተጭነን በመጫወት እነሱ ብዙ ስህተት እንዲሰሩ አድገናል ነገር ግን ያገኘናቸውን ዕድል መጠቀም አልቻልንም አጨራረስ ግን ብዙ ጊዜ የሚጠይቅ ነገር ነው ጎል ማስቆጠር በቀላሉ የሚመጣ ነገር አይደለም በማለት ገልጿል።
ከተጨሩ ነገሮች መካከል የስነ ልቦና ጉዳይ አንዱ ነው ደፍረ ወደፊት ማጥቃት ጀምረናል ካለፈው ጨዋታ በአንድ ጊዜ በአንድ ቀን ልምምድ የተሻለ ለውጥ አምጥተናል እኛ በሁለት ጨዋታ ሁለት ጎል አስቆጥረናል እነሱ አንድ ጎል ነው ያስቆጥሩት በዛ ደረጃ ከተመለከትን እኛ የተሻለን ነን እየተሻሻለ የሚሄድ ቡድን ነው ሲል ዋና አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ ገልጿል።

