ወላይታ ድቻ ስፖርት ክለብ አዲስ ስራ አስኪያጅ ሾሟል!

ወላይታ ድቻ ስፖርት ክለብ ከታዳጊ እግርኳስ ፕሮጄክቶች ጀምሮ እስከ ዋናው የወንዶችና የሴቶች እግርኳስ ቡድን ድረስ ያሉ ስራዎች ይበልጥ እንዲጠናከሩ እንዲሁም የቮሊቦል ቡድኑ የያዘበትን አስደናቂ የውጤት ጉዞ ለማስቀጠል በማሰብ አቶ ዋሲሁን ወልደዮሐንስን አዲስ ስራ አስኪያጅ በመሆን መሾሙን ይፋ አድርጓል ።

አቶ ዋሲሁን ወልደዮሐንስ የመጀመሪያ ዲግሪ በስፖርት ሳይንስ እንዲሁም ሁለተኛ ዲግሪ በቢዝነስ አድሚኒስትሬሽን የያዘ ሲሆን በ2017 እና 2018 በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ የውድድር ኮሚቴ በመሆን በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን መሥራት ችሏል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *