የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕዝዳንት አቶ ኢያሳያስ ጅራ በጅማ ከተማ ከሚገኙ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ የጨዋታ አመራሮች እና ከተሳታፊ ክለቦች ጋር ውይይት አድርገዋል።

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ በጅማ ከተማ ተገኝቶ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ተሳታፊ ክለቦች እንድሁም ከጨዋታ አመራሮች ጋር ውይይት ያደረጉ ሲሆን በጅማ ከተማ በተካሄደው የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ምድብ ሀ በዳኝነት ረገድ የተሻለ አፈፃፀም መታየቱንና ልበረታታ የሚገባ ጉዳይ መሆኑን በውይይቱ መድረክ አንስተዋል።

ከክለቦች ጋር በነበረው ውይይት የተሻለ ሥራዎች የሚሰሩ ክለቦች ወደፊት እንደሚሄዱና በተለይ ደግሞ በንግግራቸው ወቅት ለእናንተ ጫማ እየሰፋን ልብስ እያሰፋን አንቆይም በስራችሁ መሠረት ወደላይ ታድጋላችሁ በስራችሁ መሠረት ወደታችም ዝቅ ትላላችሁ ከደንብ ውጭ ምንም አይነት አሠራር እንደማይኖርና ክለቦችም በዝህ ልክ ትኩረት እንዲያደርጉ ገልፀዋል።

