ከፍተኛ ሊግ | ቦዲቲ ከተማ አዳዲስ ተጨዋቾችን አስፈርሟል!

በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ምድብ ለ ጅማ ስታዲየም አሥር ጨዋታዎችን አድርጎ 8 ነጥቦች በመሰብሰብ 10ኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ቦዲቲ ከተማ ሁለተኛ ዙር ተፎካካሪ ሆኖ ለመቅረብ አዲስ ዋና አሰልጣኝ የሾመ ሲሆን አዳዲስ ተጨዋቾችን አስፈርሟል።

ከዝህ ቀደም በወላይታ ድቻ ተስፈኛ ከዛም 2016 ከኢትዮጵያ ቡና  ተስፋ ቡድን ጋር ከ20 ዓመት በታች ፕሪሚየር ሊግ ሻምፕዮን መሆን የቻለው የተከላካይ አማካይ ወደ ዋናው ቡድን ማደግ የቻለው ቴዎድሮስ በለጠ ቦዲቲ ከተማን ተቀላቅሏል።

ከዝህ ቀደም በዱራሜ ከተማ እንድሁም አክሱም ከተማ መጫወት የቻለው አጥቂው ትዕዛዙ መንግስቱ (ዱንጋ) ለቦዲቲ ከተማ ፊርማውን አኑሯል።

ከዝህ ቀደም ዱራሜ ከተማ ፣ መንጌ ቤላሻንጉል እና አክሱም ከተማ መጫወት የቻለው አጥቂው ምትኩ በርጉዳ ለቦዲቲ ከተማ ፊርማውን አኑሯል።

ከዝህ ቀደም ነገሌ አርሲ ከዛም ደብረ ብርሃን ከተማ መጫወት የቻለው ተከላካዩ አባተ አለሙ ለቦዲቲ ከተማ ፊርማውን አኑሯል።

ከዝህ ቀደም ቦዲቲ ከተማ ፣ ደብረ ብርሃን ከተማ እና ጋሞ ጨንቻ መጫወት የቻለው የመስመር አጥቂ እንድሁም አማካይ ሆኖ መጫወት የሚችለው ሙሉቀን ተስፋዬ ለቦዲቲ ከተማ ፊርማውን አኑሯል።

ከዝህ ቀደም ቦዲቲ ከተማ ከዛም ያለፉትን ዓመታት በደብረብርሃን ከተማ መጫወት የቻለው የመስመር ተከላካይ ከድር ዳንሳ ለቦዲቲ ከተማ ፊርማውን አኑሯል።

ከዝህ ቀደም በቦዲቲ ከተማ ከዛም ጋሞ ጨንቻ እንድሁም በድጋሚ ተመልሶ እየተጫወተ የሚገኘው አማካዩ አቦነህ ገነቱ እንድሁም ዮሐንስ ዮሴፍ ለቦዲቲ ከተማ ፊርማውን አኑሯል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *