ከአብዲ ቦሩ እስከ ቅዱስ ጊዮርጊስ

የቅዱስ ጊዮርጊስ አስደናቂው አማካይ ሁለገቡ ተጨዋች ሐብታሙ ጉልላት ተወልዶ ያደገው በሸገር ከተማ በዓለም ገና (ኬንተሪ) አከባቢ ሲሆን ዕድሜው አሥር ዓመት አከባቢ ሲደርስ በዛው አከባቢ በሚገኘው አብዲ ቦሩ እግር ኳስ ፕሮጀክት ካሁኑ የፉሪ ክፍለ ከተማ እና የአብዲ ቦሩ እግር ኳስ ፕሮጀክት መስራች ከአሰልጣኝ አበበ ተስፋዬ ጋር የእግር ኳስ ስልጠና ጀመረ።

አሰልጣኝ አበበ ተስፋዬ በወቅቱ ስለነበረው ነገር ሲያስታውስ በአንድ ኳስ ብቻ ነበር የሚንሰራው በተስፋ ነው የጀመርኩት ቢያንስ ከምሰለጥኑ ተጨዋቾች የፕሮጀክቱን ስም የሚያስጠሩ እንድሁም ከራሳቸው አልፈው የቤተሰባቸውን ህይወት የሚለውጡ ተጨዋቾችን ለመፍጠር ነው።

ሐብታሙን ጉልላት ከ20 ዓመት በታች ቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ ከተቀላቀለ በኋላ ዕድገቱ እጅግ ፈጣን ነው በ2017 ወደ ዋናው ቡድን ካደገ በኋላም ከቡድኑ ጋር ለመላመድ አልተቸገረም።

በ19ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ህዳሴ ዋንጫ አስደናቂ ብቃት ማሳየት የቻለው ወጣቱ የአማካይ ስፍራ ተጨዋች በቦታ ልዩ ችሎታ እያሳየ የሚገኝ ሲሆን ከበርካታ እግር ኳስ ተመልካቾች ሙገሳን እያገኘ ይገኛል።