ለእኔ እግር ኳስ ማለት እየተዝናናሁ የሚጫወትበት ትልቅ ህይወቴ ነው መሳይ ዮሐንስ

ሻምፒዮን እንደምንሆን ሙሉ እምነት አለኝ የሲዳማ ቡና የጎል አዳኝ መሳይ ዮሐንስ !

ዳጉ ስፖርት ከሲዳማ ቡና ተስፋ ቡድን  አጥቂ መሳይ ዮሐንስ ጋር ቆይታ አድርጓል።

የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ፕሪምየር ሊግ ሲዳማ ቡና ከሀዋሳ ከተማ ጋር በነበረው ጨዋታ የማሸነፊያ ሁለት ግቦችን ማስቆጠር ችለሃል እና ምን አይነት ደስታ ተሰማክ?

መሳይ ዮሐንስ የማሸነፊያ ሁለት ጎሎች እኔ በማስቆጠሬ እና ቡድናችን ወደ ፍፃሜ በማለፉ በጣም ደስተኛ ነኝ ይሄ ጨዋታ የደርቢ ጨዋታ እንደመሆኑ ትልቅ ስሜት ነበረው በማለት የጨዋታውን ክብደት ገልጿል።

ሲዳማ ቡና ሁለተኛ ዙር የውድድር ጊዜ ላይ በርካታ ጫና ነበረባችሁ በተጫዋቾችም ጉዳት በኩል ያንን ነገር እንዴት መቋቋም ቻላቹ?

በሁለተኛው የውድድር ጊዜ ላይ በጉዳት ምክንያት ብዙ ተጫዋቾችን አጥተናል  በቡድናችን ላይ የነበሩትን ጫናዎች በሙሉ ተቋቁመን እዚህ ለመድረስ የፈጣሪ እገዛ እና አሰልጣኝችን ትልቅ ጥንካሬ ሆኖልናል።

ዛሬ እስከ 89ኛው ደቂቃ ድረስ 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት ላይ ነበርን በ90ኛ ደቂቃ ላይ የማሸነፊያዋን ጎል ሳስቆጥር  እኔ ወደ ሜዳ ከገባሁ ጀምሮ ጎል ማግባት እንዳለብኝ አውቅ ነበር ፈጣሪ ረድቶኝም ያንን ማሳካት ችያለሁ ሜዳ ውስጥ ለጎል የሚሆኑ አጋጣሚዎችን ሳገኝ ጎል እንደማስቆጥር ሙሉ በራስ መተማመን አለኝ ሲል ተስፈኛው አጥቂ መሳይ ዮሐንስ ገልጿል።

ጎል ለማስቆጠር የአየር ላይ ኳሶች ይልቅ በመሬት ላይ ያሉ ኳሶች ይሻለኛል
ለምን ቢባል መሬት ለመሬት የሚመጡ ኳሶችን እንደፈለኩ አድርገ ለመምታት ስለሚመቸኝ እነሱን በቀላሉ ማስቆጠር እችላለው ከግብ ጠባቂ ጋር አንድ ለአንድ ስንገናኝ ደግሞ መጀመሪያ ሰፋ ያለ ቦታ ካገኘሁ ቀና ብዬ አይቼ ካልሆነም ግብ ጠባቂውን አልፌ ማስቆጠር ይቀለኛል ሲል መሳይ ተናግሯል።

ስለ ጎል ማስቆጠር ኃላፊነት

አጥቂ እንደመሆነ ጎል የማስቆጠር ዕድሎች ሲያመልጡኝ ኳስ እንደመሆኑ መጠን ስህተቶች እንደሚፈጠሩ አውቃለሁ ከዛ ስህተት ተምሬ በሚቀጥለው  ጨዋታ የተሻልኩ ሆኜ ለመቅረብ እዘጋጃለሁ ደጋፊዎች ዛሬ ሲታስቆጥር ያጨበጭቡልሃል ነገ ላይ ግን ያንን ሳታደርግ ስትቀር ይተቹሃል እኔ ግን ሁልጊዜ የአሰልጣኜን ምክር ነው የሚሰማ ሲል ተናግሯል።

በሜዳ ላይ ከሚገኙ አማካዮች ጋር ያንተ የጨዋታ ግንኙነት ምን ይመስላል?

አሁን አሁን ከቡድኑ አማካዮች ጋር ያለን ግንኙነት በጣም እየተሻሻለ መጥቷል አንድ ሁለት ኳስ ነካክተን ወደፊት እንድንገፋ እና እኔም ጎል እንዳስቆጥር ያግዙኛል በቡድኑ ውስጥ ያሉ ወጣት አጥቂዎችንም ጠንክረው እንዲሰሩ እና ከእኔ የተሻሉ መሆን እንደሚችሉ እመክራቸዋለሁ ውድድሩን በ17 ጎሎች ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ ሆኜ እየመራሁ እገኛለሁ ሲል መሳይ ዮሐንስ ገልጿል።

ስለ ፍፃሜው ጨዋታ ?

የፍፃሜው ጨዋታ ከጠንካራው ወላይታ ድቻ ጋር እንጫወታለን እነሱ በጣም ጠንካራ ቡድን ቢሆኑም እኔም ሆንኩኝ የቡድኔ አባላት ሻምፒዮን ለመሆን ተዘጋጅተናል በግሌ በጨዋታው ጎል ለማስቆጠር የሚችለውን ሁሉ አደርጋለው ያለ ሲሆን የዘንድሮ ውድድር ከጀመረበት ቀን አንስቶ እያንዳንዱን ጨዋታ እንደ ፍፃሜ እያየን ስለመጣን በቀጣዩ ጨዋታም ሻምፒዮን እንደንንሆን ሙሉ እምነት አለኝ ሲል ተናግሯል።

ስለ አሰልጣኝ አመሃ ዘውዴ ምን ትላላህ?

አሰልጣኛችን አመሃ ዘውዴ ለእኔ እንደ አሰልጣኝ ብቻ ሳይሆን እንደ አባት እና እንደ ወንድም ሆኖ በብዙ ነገር ይረዳኛል ለዚህም ከልብ አመሰግነዋለሁ እሱ ለእኔ ብቻ ሳይሆን ለጠቅላላ የቡድን አባላት እንደ አባት በመሆኑ፣ ይህ የቡድን አንድነታችን (Team spirit) ለስኬታችን ትልቁን ሚና ተጫውቷል ሲል ገልጿል።

በመጨረሻም መሳይ ዮሐንስ ለእኔ እግር ኳስ ማለት እየተዝናናሁ የሚጫወትበት ትልቅ ህይወቴ ነው በማለት ሀሳቡን ቋጭቷል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *