ጨዋታው አላለቀም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ !

ዋና አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ በመጀመሪያ ለውጤቱ መምጣት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጨዋቾች በስነ-ልቦና በዲሲፕሊን መስራት የሚገባቸውን ነገር ሰርተው ለዚህ ድል አብቅተውናል ሲሉ ተጨዋቾችን አመሰግናለው።

የቴክኒክ ስታፉና አመራሩ ደግሞ ሙሉ በሙሉ አስተዋጾ አለው እዚህ ላይ የነኝህ ሁላ ውጤት ነው የኔ ውጤት ሳይሆን ይሄ የኢትዮጵያ ህዝብ ውጤት ነው በዚህ ደረጃ ላይ መክፈል የሚገባው መስዋዕትነት ተከፍሏል በቀላሉ የተገኘ ውጤት አይደለም ሲሉ ተናግረዋል።

ሀገራዊ የሆኑ መነቃቃቶች እንዲፈጠሩ አድርገንበታል ተጨዋቾች ሜዳ ከመግባታቸው በፊት የኢትዮጵያዊነት ማንነታችንን ማሳየት እንደሚገባን ፣ ተስፋ እንደማንቆርጥ ሳኦቶሜ ባለሜዳ እንደመሆኑ መጠን በሜዳቸው ጨዋታውን ለመጨረስ ከፍተኛ መስዋዕትነት እንደሚከሉ ስላወቅን እኛ ደግሞ ከዝህ የተሻለ ውጤት ወደ ሀገራችን ይዘን መሄድ ስላለብን ማድረግ የሚገባን ሁላ አድርገናል ብዬ እገምታለሁ ሲሉ ገልፀዋል።

ውጤቱ የጋራ ውጤት ነው የተጨዋቹ እንድሁም የቴክኒክ አመራር ውጤት ነው እንጂ የኔ ውጤት አይደለም በመጨረሻም ደግሞ ከፍ የሚለው የኢትዮጵያ ባንዲራ በመሆኑ በጣም ደስተኛ ብለዋል።

ሜዳ ላይ የገጠመን የጠበቅነውና የተነጋገነው ነው የመጀመሪያውን 15 ደቂቃ ተጭነው እንደሚጫወቱ ገምተን ነበር ተጨዋቾቹ ገብቷቸዋል አድርገውታል 15 ደቂቃ ጫና ከተቋቋምን በኋላ ወደራሳችን ጨዋታ በመምጣት ስህተት እንዲሰሩ አድርገን ስህተቶቻቸውን ተጠቅመንበታል በማለት ተናግሯል።

ልምድ ያላቸው ልምዳቸውን በማካፈል ወጣቶቹ ደግሞ ያንን በመከተል በጋራ የተሰራ የቡድን ውጤት እንደተመዘገበ ገልፀዋል።

ተጨዋቾቻችን በየትኛውም መንገድ ያላቸውን ለመስጠት ዝግጁ ናቸው የሀገራዊ ፍቅር ከፍ ያለ ነው የመጀመሪያ ጨዋታ አልቋል ጠንካር ያለ ጨዋታ የሚያጋጥመን አሁን ነው ሳኦቶሜ ከሞሮኮ እስከ ድሬዳዋ ዝምብለው አይመጡም አማራጭ የላቸው ለማሸነፍ ነው የሚመጡት ስለዝ ከበፊቱ የተሻለ የስነ-ልቦና የዲስፕሊን ዝግጅት የሚያስፈልገው አሁን ነው ሲሉ ገልፀዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *