የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ምድብ ሀ ሁለተኛ ቀን ውሎ!

የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ 15ኛ ሳምንት ሁለተኛ ቀን ሁለት ጨዋታዎች በጅማ ስታዲም ዛሬ ከሰዓት ተደርገዋል።

7:30 በተጀመረው ጨዋታ ንብ 2ለ1 ቡራዩ ክፍለ ከተማን ሲያሸንፍ በጨዋታው ለንብ እግር ኳስ ክለብ ማኑሄ ጌታቸው በመጀመሪያ አጋማሽ 23ኛ ደቂቃ እንድሁ ጌታዓለም ማሙዬ በሁለተኛ አጋማሽ 68ኛ ደቂቃ ማስቆጠር የቻለ ሲሆን ለቡራዩ ክ/ከተማ ሊሬ አባይነህ 90+4 በጭማሪ ደቂቃ ጎል አስቆጥሯል ።

የአሰልጣኝ ኢዮብ ማሌ (አሞካቺ) ንብ ጨዋታውን ማሸነፉን ተከትሎ ነጥቡን 23 በማድረስ ካለፈው ሳምንት አንድ ደረጃ ከፍ በማለት 4ኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ሲችል በውድድር ዓመቱ ያሸነፋቸውን የጨዋታ ብዛት ወደ 6 ከፍ አድርጓል።

ቡራዩ ክ/ከተማ በ17 ነጥብ 7ኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ ሲሆን በውድድር ዓመቱ 6ኛ ሽንፈቱን አስተናግዶ መውጣት ችሏል።

ተጠባቂ የ10:00 ሰዓት ጨዋታ ባቱ ከተማ ከ ቤንች ማጂ ቡና ጋር ያደረጉት ጨዋታ ቤንች ማጂ ቡና 3ለ0 በሆነ ውጤት አሸንፏል ።

ባቱ ከተማ ሽንፈት ማስተናገዱን ተከትሎ ከጋሞ ጨንቻ ጋር ያለው የነጥብ ልዩነት ማጥበብ ሳይችል ቀርቷል።

የማሸነፊያ ጎሎችን በ50ኛው ደቂቃ አብዱላዚዝ ዑመር በ83ኛ ደቂቃ መርሁን መንቴ እና በ89 ደቂቃ ሰለሞን ጌታቸው አስቆጥረዋል።

ቤንች ማጂ ቡና ጨዋታ ማሸነፋን ተከትሎ ነጥቡን 21 በማድረስ 6ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *