የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ምድብ ሀ 16ኛ ሳምንት ሁለተኛ ቀን 4:00 ላይ ነቀምቴ ከተማን ከ ቡራዩ ክ/ከተማ አገናኝቷል።
ጨዋታውም በመጀመሪያው አጋማሽ በኳስ ቁጥጥሩ ሁለትም ቢድኖች ተመጣጣኝ እንቅስቃሴ የበራቸው ቢሆንም የነበሩ ቢሆንም በሁለቱም ቡድኖች በኩል ግብ ለማስቆጠር ተቸግረው ተስተውለዋል።
በመጀመሪያ አጋማሽ በዋና አሰልጣኝ ቾምቤ ገ/ህይወት የሚመራው ነቀምቴ ከተማ በእስጥፋኖስ ተማም አማካኝነት ሁለት ጊዜ ከረጂም ርቀት ወደ ግብ የተሞከሩ ኳሶች በቡራዩ ክፍለ ከተማ ግብ ጠባቂ በልስቲ ቀረብኝ ግብ እንዳይሆኑ ማድረግ የቻለ ሲሆን በዋና አሰልጣኝ አይናለም ግርማ (ቦረና) የሚመራው ቡራዩ ክ/ከተማ ከቀኝ መስመር ተስፋሁን ሙሉጌታ የተሻገረውን ኳስ ጴጥሮስ ገዛኸኝ ከነቀምቴ ከተማ ግብ ጠባቂ ማቴዎስ ሰለሞን ጋር ፊትለፊት ተገናኝቶ የሳተው ኳስ ተጠቃሽ ነበር።

ሁለተኛው አጋማሽ ላይ 66ኛ ደቂቃ ቡራዩ ክፍለ ከተማ ወጋየሁ ብርሃኑ ለሊሬ አባይነህ ለማሻገር ሲሞክር መሃል ተከላካዩ ሰጠኝ ኢየሱስ የናካው ኳስ በራሱ ላይ ጎል ላይ ተቆጥሮ ጨዋታው በቡራዩ ክ/ከተማ 1ለ0 አሸናፊነት መጠናቀቅ ችሏል።
7:30 ላይ የካ ክ/ከተማን ከ ቤንች ማጂ ቡና አገናኝቷል።
በዋና አሰልጣኝ ያሬድ ቶለራ የሚመሩት የካ ክ/ከተማዎች በጨዋታው 24ኛ ደቂቃ ላይ በእዩኤል አበባየሁ ጎል ቀዳሚ መሆን ብችልም ግን መሪነታቸው መቀጠል ብችልም መደበኛው ደቂቃ ልጠናቀቅ ሁለት ደቂቃዎች ብቻ በቀረበት ሰዓት መሐመድ ናስር ለቤንች ማጂ ቡና ጎል አስቆጥሮ ሁለቱ ቡድኖች 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት ወደ መልበሻ ክፍል አምርተዋል።

ሁለተኛ አጋማሽ 53ኛ ደቂቃ ላይ ፍሬገነት ኤርሚያስ በግንባሩ ያስቆጠረው ጎል ዳግም የካ ክ/ከተማን ወደ መሪነት የመለሰ ኳስ ሲሆን 89ኛ ደቂቃ ከ29 ያህል ሜትር ርቀት ላይ የግብ ጠባቂውን አብነት ይስሃቅ አቋቋም ተመልክቶ ከመልስ ውርወራ ያገኘውን ኳስ በግሩም ሁኔታ በማስቆጠር የካ ክ/ከተማ ጨዋታውን 3ለ1 አሸፎ እንድወጣ ማድረግ ችሏል።

ተጠባቂው የ16ኛ ሳምንት ጨዋታ ባቱ ከተማን ከንብ (አየር ኋይል) ያደረጉት ጨዋታ በንብ 1ለ0 አሸናፊነት ተጠናቋል።
ጋሞ ጨንቻ ከሐረር ከተማ ጋር ያደረገው ጨዋታ በአቻ ውጤት መጠናቀቁን ተከትሎ የነጥብ ልዩነቱን ማጥበብ የሚችልበት አጋጣሚ ባቱ ከተማዎች ሳይጠቀሙ ቀርተዋል።

በዋና አሰልጣኝ ኢዮብ ማዓሌ (አሞካቺ ) የሚመራው ንብ ክለብ 20ኛ ደቂቃ ማኑሄ ጌታቸው ያቀበለው ኳ አጥቂው ባዬ ገዛኸኝ ከ35 ሜት ርቀት አከባቢ አክርሮ በመምታት ባስቆጠረው ግሩም ጎል ጨዋታው 1ለ0 አሸንፏል።
ዋና አሰልጣኝ ራማቶ መሐመድን በቅጣት ምክንያት ያጣው ባቱ ከተማ ተከታታይ ሽንፈት ለማስተናገድ ሲገደድ ንብ ነጥቡን ወደ 26 ከፍ ማድረግ ችሏል።
ባቱ ሽንፈት ማስተናገዱን ተከትሎ የካ ክ/ከተማ 2ኛ ደረጃን ተረክቧል።

