የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ 17ኛ ሳምንት ምድብ ለ መረጃዎች

የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ምድብ ለ 17ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ዛሬ በሀዋሳ አርቴፊሻል በሚካሄዱ ሶስት ጨዋታዎች ጅማሮን ያደርጋል።

የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ምድብ ለ 4:00 ሰዓት አዲስ አበባ ከተማ ከ መንጌ ቤላሻንጉል የሚጫወቱ ሲሆን አዲስ አበባ ከተማ እስካሁን አንድም ጨዋታ ማሸነፍ ያልቻለ ቡድን ነው ።

አዲስ አበባ ከተማ 6 ጨዋታዎችን ተሸኝፎ 8 ነጥቦች በመሰብሰብ 11ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

መንጌ ቤላሻንጉል 22 ነጥቦች በመሰብሰብ 3ኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ ሲሆን ደሴ ከተማና ሀላባ ከተማ እስክጫወት ጨዋታውን ማሸነፍ የምችል ከሆነ ነጥቡን ማጥበብ የምችለበት አጋጣሚ ልፈጥር ይችላል።

ሁለተኛ ጨዋታ 7:30 ቢሾፍቱ ከተማ ከ ደሴ ከተማ የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠባቂ ሲሆን ሁለቱም ቡድኖች ሀዋሳ አርቴፊሻል ሜዳ ያደረጓቸውን ጨዋታዎች ያልተሸነፉና በተመሳሳይ አንድ አቻ ውጤት ሲያስመዘግቡ ቀሪ ጨዋታቸውን አሸንፈዋል።

ደሴ ከተማ ጨዋታውን ማሸነፍ የሚችል ከሆነ ነጥቡ 32 በማድረስ መሪው ሀላባ ከተማ እስክጫወት በጊዜያዊነ የሊጉ መሪ የሚሆንበት ዕድል ሲኖረው 4ኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ቢሾፍቱ ከተማ ጨዋታውን ማሸነፍ የሚችል ከሆነ ነጥቡን ወደ 24 ከፍ ማድረግ የሚችልበት አጋጣሚ ይፈጠራል።

10:00 ሰዓት ጨዋታ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ከ ሀላባ ከተማ ጋር የሚያደርጉት ጨዋታ ሲሆን ሀላባ ከተማ 31 ነጥቦች በማስመዝገብ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ምድብ ለ መሪ ሲሆን ንፋስ ስልክ ላፍቶ በ14 ነጥብ 8ኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ ቡድን ነው።

ንፋስ ስልክ ላፍቶ በ16ኛ ሳምንት ደሴ ከተማን ነጥብ ማስጣሉ የሚታወስ ሲሆን ሀላባ ከተማ ከመመራት ተነስቶ አዲስ አበባ ከተማን 2ለ1 ማሸነፉ የሚታወስ ነው።

17ኛ ሳምንት ነገም የሚቀጥል ሲሆን
7:30 ቦዲቲ ከተማ ከ ደብረ ብርሃን ከተማ
10:00 ሱሉልታ ክ/ከተማ ከ አዲስ ከተማ ክ/ከተማ ይጫወታሉ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *