ብዙ መሻሻል የሚገባቸው ነገሮች አሉ እኛ የሰራነው በልጆች ጭንቅላት ላይ ነው ሀገራዊ ስሜት 130 ሚሊዮን ህዝብ አደራ ነው የተሸከማችሁት ሰው ታሪክ ሲሰራ ይሞታል እናንተ በህይወት እያላችሁ ታሪክ ስሩ ነው ያልኳቸው ሲል ገልፀዋል ።
በአምስት ደቂቃ ውስጥ ቴክኒክ እና ታክቲክ ልታስተምር አትችልም ግን ልታነሳሳ ትችላለህ ስል ተናግሯል።
ዛሬ ጎል ካስቆጠርን በኋላ ወደ ግላዊ ጨዋታ ተመለሱ ይሄ ፕሮፌሽናል አካሄድ አይደለም ግን መሻሻል ይችላል ከዝህ በኋላ እንሰራለን እንደ ቡድን ነው የተጫወትነው እንደ ቡድን በአንድነት ነው ያሸነፍነው ብሏል።
ተጨዋቾች ምርጫ ስንመረጥ በብዛት ልምድ ያላቸው ተክለሰውነታቸው ጥሩ የሆኑትን ነው እንጂ ሌሎች ነገሮች ለወደፊቱ ይኖራሉ በተለይም በማጥቃት ላይ ያሉ ብዙ ችግሮች አሉበን እነሱን እናስተካክላለን ሲል ተናግሯል።
እንደ ሀገር 130 ሚሊየን ህዝብ አለን 10 ሺ ሰው የሚይዝ ስታዲየም ሊኖረን ይገባል ሊታሰብበት ይገባል የሀገር ክብር ነው ውድድር ውስጥ እስካለን ጊዜ ድረስ ከተወዳደር ጊዜ ድረስ አንዱ መስፈርት ሜዳ ነው ብዙ ገንዘብ እያስወጣብ ነው ብዙ የጉዞ ወጪ እያወጣን ነው ህዝባችንም ለ5 ዓመት ብሔራዊ ቡድኑን በሜዳው የማያይበት አጋጣሚ ተፈጥሮ ነበር እኛ ህዝብ ለማገልገል ሜዳ የገባን አገልጋዮች ህዝቡ ብሔራዊ ቡድኑን ማየት ይፈልጋል ሜዳዎች መሠራት አለባቸው ብሏል።
የትውልደ ኢትዮጵያዊ ተጨዋቾች ጉዳይ በመንግስቱ ደረጃ መመለሴ የሚገባ ጉዳይ ነው ትውልድ ኢትዮጵያኖ ተወዳድረው የተሻለው ከሆኑ እንዲጫወቱ ቢደረግ እኛም የት እንዳለን ማወቅ እንችላለን ይሄ የተሻለ ሀሳብ ነው ብሏል።
በሌላው ዓለም እየተከፈላቸው ወይም እየተማሩ ወይም እየሰለጠኑ ለኢትዮጵያ ልጫወት ሲል ይሄ ትልቅ ክብር ነው ለሎች ሀገራት የሚያደርጉትን እኛ ሀገር እንዳናደርግ ምንድነው ያቃተን ለምሳሌ ኤርትራ ማድረግ ከቻለች እኛ ምን ያቅተናል እንደ ስታዲየም ሁሉ መንግስት መፍታት የሚገባው ጉዳይ ነው ብሏል።
በእኔ በኩል ዛሬ ለመጀመሪያ ለጠየከኝ ጥያቄ ቅያሬ የሚለው ለምሳሌ ከነዓን ማርክነህ አይነቱ ትናንትና ተጎድተው ከልምምድ ወቷል እንዲገባ ያደረገው የደጋፊዎች ሜዳ መግባት ነው ያነሳሳው የድሬዳዋ ህዝብን እናመሰግናለን ሲል ተናግሯል።
ብዙ ሰው እንትናን ለምን ቀይሮ አያስገባውም ይላል ይሄ በላብና በደም የመጣ ውጤት ነው ድሬዳዋ ላይ ነው የተጫወትነው ታሪክ ሰርተን መሄድ ፈለግን ታስታውሱ ከሆነ ባህርዳር ላይ ምንም ጨዋታ ተሸንፈን አናውቅም እንደዛ በድሬዳዋ ላይም ያንን ነገር ማስቀጠል ስለፈለግን ነው ሜዳ የመጣው ህዝብ ተደስቶ መሄድ አለበት ብዬ አስባለው ብሏል።
ሰዎች የሚያዩት ብሔራዊ ቡድን ማሰልጠንህን ነው ከጀርባ ያለውን ጫና ቀላል አይደለም መሸነፍን ባህል አድርገን ነበር ይሄን ለማሻሻል እና ባህል እንዳይሆን ለማድረግ አንድ ለመፍጠር የሞከርኩት ራሴን ዝቅ ማድረግ ነው ብሏል።
ከ70 ደቂቃ በኋላ ብሔራዊ ቡድን ይደክማል አቅም የለውም የምል ወረዎች ነበሩ አሁን ግን ያን አላየንም የደከሙት በስነ-ልቦና ነበር ለማነቃቃት ነው የሞከርነው ሳንጫወት መሸነፍ የለብንም የክለብ ማሊያ አውልቀን የብሔራዊ ቡድን ማሊያ እንድለብሱ ነው ያደረግነው ስል ተናግሯል።
ሁሉም ሰው ያሰበው የመጀመሪያውን 20 ደቂቃ ሳኦቶሜ ያጠቃል ብሎ ነው ሰው የጠበቀው እኛ ግን ያንን ገልብጠን ማጥቃት የጀመርነው እኛው ነው ጎልም አስቆጥረናል የህብረት እና የአዕምሮ ሥራ ነው የሰራነው ብሏል ።
ስለ ድሬዳዋ ሜዳው ለመግለፅ ልምድ ይፈልጋል በልምምድ ጊዜ እንኳን በርካታ ተጨዋቾቻችን ጉዳት አስተናግደዋል ከሳር ወደዝህ መምጣችን ትንሽ አስቼግሮናል ልምድ ይፈልጋል ኳስ ለማንከባለል ግን ምቹ ነው ሲሉ ሀሳባቸውን ቋጭተዋል።
