የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በ2027 የአፍሪካ ዋንጫ ቅድመ ማጣርያ ከሳኦቶሜ እና ፕሪንሲፔ ጨዋታ በፊት ዛሬ በጁፒተር ሆቴል ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል!

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በ2027 የአፍሪካ ዋንጫ ቅድመ ማጣርያ ከሳኦቶሜ እና ፕሪንሲፔ ጋር ለሚያደርገው ጨዋታ ያደረገውን ዝግጅት እንዲሁም ወደ ሞሮኮ የሚያደርገው ጉዞን አስመልክቶ ዋና አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳሕሌ እና የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌፍሬሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ባሕሩ ጥላሁን ዛሬ በጁፒተር ሆቴል ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።

ከሳኦቶሜ እና ፕሪንሲፔ ጋር ያለው ጨዋታ የጥሎ ማለፍ ጨዋታ ነው የጥሎ ማለፍ ጨዋታ የራሱ ባህሪ አለው ለተጨዋቾች ልምድ የሚንሰጥበት አይደለም ከዛ በመነሳት ይጠቅማሉ ብለን ያሰብናቸውን ተጨዋቾች መርጠናል ስሉ ዋና አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ ገልፀዋል

ጥሎ ማለፉ እንደመሆኑ መጠን ልምድ ያላቸውን ፣ ጫናን የለመዱ ፣ የጉዞ ልምድ ያላቸው ተጨዋቾች እና በሰው አገር በተለያየ አየር ንብረት የመጫወት ልምድ ይጠይቃል ብለዋል።

በተጨማሪም ያሉን ጊዜዎች እንደምታቁት በአጭር ጊዜ ውስጥ የሚሰሩ ስራዎች ስለነበሩ የምንመርጣቸው ልጆች በአካል ብቃት የተሻሉና ብቁ መሆን ነበረባቸው ያንንም ለማሟላት የመጨረሻውን ቢያንስ አምስት ጨዋታው የስድስት ጨዋታዎችን በተከታታይ የተጫወተው መሆን ነበረበት ምክንያቱም አካል ብቃት ወሳኝነት ስለነበረው በአጭር ጊዜ የቅንጅት ሥራ ስለሆነ እነዛን ታሳቢ በማድረግ ተጨዋቾን መምረጣቸውን ገልፀል።

በዛም መካከል ደግሞ አቅማቸውን ያሳዩ አንዳንድ ወጣት ተጫዋቾች እንዲመረጡ ሆኗል ምንም እንኳን ልምድ ባይኖራቸው ብለዋል።

በጤንነት ደረጃ እስካሁን ድረስ ምንም ጉዳት የለንም ሁሉም ተጨዋቾች በጥሩ ጤንነት ላይ እንደሚገኙ ገልፀዋል።

ባህሩ ጥላሁን

ከጨዋታው ጋር በተያያዘ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የሠራቸው አስተዳደራዊ የሆኑ ሥራዎችን ለብሔራዊ ቡድኑ አስፈላጊ የሆነውን ትጥቅ ከማሟላት ጀምሮ ሊያርፉበት የሚችሉ ሆቴሎችን ማመቻቸት ጀምሮ የሜዳ ፋሲሊቲ ከማመቻ ጀምሮ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን እነዚህን ክንዋኔዎች በመጀመሪያ ደረጃ ጀምሮ አከናውኗል ካሉ በኋላ ከዛ በተጨማሪም ደግሞ ሁለት በውጭ ሀገር የሚጫወቱ ተጫዋቾች ጥሪ እንዲተላለፍላቸው በተገለፀው መሰረት ከነዓን ማርክነህ እና ለጋቶች ፓኖም ቡድኑን እንድቀላቀሉ ጥሪ ማድረጋቸውን ገልፀዋል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከአምስት አመት በኋላ በሜዳው በዝግ (ያለደጋፍም ቢሆንም) በሜዳ ጨዋታውን ማድረግ የሚችልበትን ሁኔታ ማመቻቸው ችለናል ለዚህም የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ክቡር ፕሬዝዳንት ኢሳያስ ጅራን ፣ የክለብ ላይሰንስንግ ዲፓርትመንት ፣ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ ፣ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ እና የድሬዳዋ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ያለቻውን ምስጋና እንድሁም አክብሮት ገልፀዋል።

ኢትዮጵያ የ2028 የአፍሪካ ዋንጫ ለማዘጋጀት ጥያቄ ካቀረቡ ሀገራት መካከል አንዷ ናት ስፖርት ፖለቲክሱ እንደሚታወቀው አንዱን እንቅፋት ልሆን የነበረው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በሀገሩ አይጫወትም እንዴት የ2028 የአፍሪካ ዋንጫ የማዘጋጀት ጥያቄ ታቀርባላችሁ የሚሉ ጥያቄዎችም በተለያዩ አካላት ከኛ ጋር የሚፎካከሩ ሀገራትም የሚያነሱት ነበሩ ስለዚህ ያንን አስተሳሰብ በመጀመሪያ ደረጃ ማስተካከል በጣም አስፈላጊ ስለሆነ እንደ ኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የድሬዳዋ ስታዲየም በካፍ እንስፌክሽን እንዲገመግም የማድረግ ሥራ መሠራቱ ገልፀዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *