ካፍ ለ10,000 ሺህ ተመልካች ፍቃድ ሰጠ !

የአፍሪካ ዋንጫ ቅድመ ማጣሪያ የመልስ ጨዋታ የኢትዮጵያ እና ሳኦቶሜ ጨዋታ ነገ በዝግ ያለደጋፊ እንዲካሄድ ካፍ ውሳኔ አሳልፎ እንደነበር የሚታወስ ሲሆን የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር በስታዲየሙ ዙርያ የተሰጡ የግምገማ አስተያየቶችን መሰረት በማድረግ በፍጥነት ለማስተካከል በወሰደው እርምጃ እንዲሁም የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጨዋታው ለተመልካች ክፍት እንዲሆን ባደረገው ከፍተኛ ጥረት የካፍ ሴኪዩሪቲ ኦፊሰር በአካል ተገኝተው ከገመገሙ በኋላ በላኩት ሪፖርት መሰረት ካፍ 10,000 ተመልካች በስታዲየም ተገኝቶ እንዲከታተል ውሳኔ ማሳለፉን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *