የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፕሬዚዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ለነገሌ አርሲ እግር ኳስ ክለብ የ50 ሚሊዮን ድጋፍ አድርገዋል።

ነገሌ አርሲ ዘንድሮ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ያደገ ሲሆን በአሁኑ ወቅት ሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ ሲሆን ክለቡ ተፎካካሪ ሆኖ የሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግን እንዲያሸንፍ ለማበረታታት 50 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አድርጓል።

የክለቡ ተጨዋቾች ቀሪ ጨዋታዎችን በትኩረት በመጫወት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አሸናፊ ለመሆን ጠንክረን መስራት እንዳለባቸው ፕሬዝዳንት ሽመልስ አብዲሳ አሳስበዋል።

የምዕራብ አርሲ ዞን ዋናአስተዳዳሪ አቶ አህማድ ሀጂ ለክልሉ ፕሬዝዳንት ላደረጉት ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *