የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የሥነ-ምግብ ባለሙያ በሆነው ዳንኤል ክብረት (ዶ/ር) አማካኝነት “አመጋገብ ለተሻለ ብቃት” በሚል ርዕስ የተዘጋጀው የስፖርት ሥነ-ምግብ መፅሐፍ በዛሬው ዕለት ካዛንቺስ በሚገኘው ጁፒተር ሆቴል ተመርቋል።

የኢ/እ/ፌ ም/ፕሬዚዳንት ዳኛቸው ንግሩ (ዶ/ር)፣ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ባሕሩ ጥላሁን፣ የፌዴሬሽን የሥራ ኃላፊዎች፣ ተጫዋቾች፣ አሰልጣኞች፣ የጨዋታ አመራሮች፣ የመገናኛ ብዙሀን እና የእግር ኳስ ቤተሰቦች በታደሙበት በዚህ የምርቃት መርሐ ግብር የመፅሐፉ አዘጋጅ የሆነው ዳንኤል ክብረት (ዶ/ር) ባደረጉት ንግግር ተጫዋቾች የተስተካከለ የአመጋገብ ሥርዓት ከተከተሉ በብቃታቸው ላይ የሚታይ ለውጥ ማምጣት እንደሚቻል የጠቆሙ ሲሆን አቶ ባሕሩ ጥላሁን በበኩላቸው የስፖርት ቤተሰቡ መፅሐፉን በአግባቡ ሊጠቀምበት እንደሚገባ ተናግረዋል።

