የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ምድብ ለ 18ኛ ሳምንት የመጀመሪያ ቀን ጨዋታዎች ዛሬ ይደረጋሉ!

የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ምድብ ለ 18ኛ ሳምንት የመጀመሪያ ቀን ጨዋታ መርሐ-ግብር መረጃዎች
ሀላባ ከተማ ከ መንጌ ቤላሻንጉል

የከፍተኛ ሊግ ምድብ ሀ መሪው ሀላባ ከተማ በ9 ነጥቦች ርቆ 3ኛ ደረጃ ላይ ከሚገኘው መንጌ ቤላሻንጉል 7:30 በሀዋሳ አርቴፊሻል ስታዲየም ይጫወታል።

በወጣቱ አሰልጣኝ በሽር አብደላ የሚመራው ሀላባ ከተማ ከተከታዩ ደሴ ከተማ ጋር ያለው የነጥብ ልዩነት 4 ሲሆን ጨዋታውን ማሸነፍ የሚችል ከሆነ የነጥቡ ልዩነቱ  ደሴ ከተማ 7 ከፍ ማድረግ የሚችልበት አጋጣሚ ልፈጠር ይችላል።

በአሰልጣኝ መሐመድ ኑር የሚመራው መንጌ ቤላሻንጉል ከስብስቡ አንፃር የተጠበቀውን ያህል መሆን ያልቻለ ሲሆን በተለይም በመጀመሪያ ዙር የጣላቸው ነጥቦች ወደ ፕሪምየር ሊጉ ለማደግ ከሚያደርገው  ፉክክር ያራቀው ይመስላል።

መንጌ ቤላሻንጉል ጨዋታውን ማሸነፍ የሚችል ከሆነ ነጥቡን ወደ 28 ከፍ ማድረግ የሚችልበትን አጋጣሚ ልፈጥር ይችላል።

17ኛ ሳምንት ጨዋታ ሀላባ ከተማ 5ለ0 ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማን ሲያሸንፍ መንጌ ቤላሻንጉ 1ለ0 አዲስ አበባ ከተማን ማሸነፉ ይታወሳል።

ሀላባ ከተማ በ34 ነጥቦ 1ኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ ቡድን ሲሆን መንጌ ቤላሻንጉል በ25 ነጥቦች 3ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠ ቡድን ሆኗል።

የመጀመሪያ ዙር ጨዋታ ጅማ ስታዲየም ሁለቱ ቡድኖች ያለ ግብ 0ለ0 በሆነ አቻ ውጤት መለያየታቸው ይታወሳል።

ደሴከተማ ከ ሶሎዳ ዓድዋ

የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ምድብ ሀ ሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ደሴ ከተማ በ13 ነጥቦች ርቆ 7ኛ ደረጃ ላይ ከሚገኘው ሶሎዳ ዓድዋ 10:00 ላይ በሀዋሳ አርቴፊሻል ስታዲየም ይጫወታል።

በዋና አሰልጣኝ ዘላለም ሽፈራው  የሚመራው ደሴ ከተማ ተከታታይ ሁለት ጨዋታዎችን በአቻ ውጤት በመለያየት ማግኘት ከነበረበት 6 ነጥብ 4 ነጥቦችን በመጣል የሊጉን መሪነት ለሀላባ ከተማ አሳልፎ ለመስጠር ተገዷል።

በአሰልጣኝ አታክልቲ በርሄ የሚመራው ሶሎዳ ዓድዋ 17ኛ ሳምንት የምድቡ አራፊ ክለብ በመሆኑ ጨዋታ አላደረገም።

ሶሎዳ ዓድዋ 16ኛ ሳምንት ጨዋታ በመንጌ ቤላሻንጉል 1ለ0 የተሸነፈ ሲሆን 15ኛ ሳምንት ጨዋታ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማን 2ለ1 ማሸነፉ ይታወሳል።

ደሴ ከተማ በ30 ነጥቦች 2ኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ ቡድን ሲሆን ሶሎዳ ዓድዋ በ17 ነጥቦች 7ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠ ቡድን ሆኗል።

የመጀመሪያ ዙር ጨዋታ ጅማ ስታዲየም ሁለቱ ቡድኖች ያለ ግብ 0ለ0 በሆነ አቻ ውጤት መለያየታቸው ይታወሳል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *