ታዳጊዎችን ማብቃት እንጂ ዋንጫ ማሸነፍ ከ20 ዓመት በታች ፕሪምየር ሊግ ውድድር ላይ ቀዳሚ ጉዳይ መሆን የለበትም ተመስገን ሎሃ

አሰልጣኝ ተመስገን ሎሃ የወላይታ ድቻ ከ20 ዓመት በታች ቡድን ዋና አሰልጣኝ ከዳጉ ስፖርት ጋር ቆይታውን አድርጓል።

ኢትዮ ኤሌክትሪክ ጋር ስለነበረው ጨዋታ ?

የመጀመሪያ አጋማሽ በሁለታችንም በኩል ከኳስ እንቅስቃሴዎች ውጪ የጎል ሙከራዎችን አላየንም እነሱም ተመሳሳይ የጨዋታ መንገድ ነው ይዘው የገቡት እና ምን ማድረግ ነበረብን የሚለውን እስከ መጀመሪያ አጋማሽ እነሱ ጉልበት እንዲያወጡ እንዲጫወቱ ፈቅደንላቸዋል ለምን እነሱ በተጫዋቹ ቁጥር እኛ ደግሞ የምንታወቅበት ጠንካራ አቅም አለን አይደክሜ ልጆች ስላሉ በሁለተኛ አጋማሽ ተጭነን ተጫውተን ጎልም አስቆጥረን አሸንፈን ወጥተናል ሲል ተናግሯል።

ጎሉ ካስቆጠርን በኃላ የደስታ አገላለፅ በርግጥ ባለፈው ከምድብ ስናልፍ ሩብ ፍፃመውን ስንቀላቀል ነው የጨረስነው የሚመስለኝ እና አሁን ግን ከፊታችን ሌላ ትልቅ ተጋድሎ የሚጠይቅ ጨዋታ አለብን በሰዓቱ ያገባነው ጎል 66ኛ ደቂቃ ላይ ስለነበር ብዙም መደሰት ልጆችን ወደ ለሌላ ነገር እንዳይወስዳቸውና እንዳንዘናጋ ለማድረግ ነው የተሞከረው ከዛ ባሻገር ተቃራኒ ቡድን ተቀያሪ ተጨዋቾች አካባቢ ስለሚሄዱ ቢያንስ ግርግር እንዳይኖር ለማድረግ ነው ግብ ጠባቂው እንኳን በደስታ አገላለፅ ወቅት እንዳይሳተፍ ያደረግኩት ሲል ሀሳቡን ገልጿል።

የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ ጥሎ ማለፍ እንደመሆኑ እጅግ በጣም ፈታኝ እና ከባድ ነበር በጣም ጥንቃቄ የሚፈልግ ጨዋታ ስለሆነም በጥንቃቄ ነው የተጫወትነው እንደ ቀድሞ ጨዋታ ሳይሆን በጥንቃቄ ተጫውትን ለፍፃሜ ደርሰናል ዋንጫውንም እናሳካለን።

ስለ ሁለተኛ ዙር ጨዋታ

በርግጥ ዘንድሮ ተዘጋጅተን ነው የመጣነው ለዚህ ውድድር ወጣት ተጫዋቾችን ነው በመጀመሪያው ዙር የያዝናቸው ትንሽ ታዳጊዎችን ነበር የተጠቀምነው በጣም ህጻናት ከ17 ዓመት በታች በቀጥታ ነበረ ያሳደግነው ሆኖም ግን ሁለተኛው ዙር ክለቦች ጋር ባየነው ዕድሜ መሠረት ሁለተኛ ዙር ተጫዋቾችንም ጨመርን አስተካክለን ሁለተኛውን ዙር ሻል አድርገን ነው ደረጃችንን የጨረስነው ጠንክረን እዚህ ቦታ እንድንደርስ ያደረገን ሁሉም ልጆች ታታሪ ፣ በጣም ተስፋ ያላቸው እና ለነገዋ ለትላልቅ ክለቦች አልፎም ለኢትዮጵያ ወሳኝ ስለሆኑ ልጆቹ ራሳቸውን ለማሳየት ገበያ ላይ እንደወጡ ማሳያ እንደሆነ ጠንክረው መስራታቸው ለዚህ ደረጃ አድርሷቸዋል ብዬ አስባለሁ ሲል ገልጿል።

የወላይታ ድቻ ተስፋ ቡድን ጥንካረው ብለህ የምታስባቸው ነገሮች ምንድን ናቸው?

ከምንም በላይ በርግጥ ለዚህ ጥንካሬያችን አንድነታችን ነው እኛ ጋር ከቡድናችን ኮቺንግ ስታፉ ጋርም ከተጫዋቹ ጋር ያለው የእርስ በርስ ግንኙነት እንደ አሰልጣኝ ብቻ ሳይሆን እንደ ወንድም ፣ እንደ ጓደኛ እና እንደ ቤተሰብ ነው እሱ ደግሞ ጠንካራ ነገር ሜዳ ላይ እንድናሳይ አድርጎናል ካየኸው ጨዋታዎችን አብዛኛው ገብቶብን ነው ቀልብሰን የምናሸንፈው ይሄ ደግሞ የአንድነት መሠረት ነው ተጫዋቾች እርስ በርስ ያላቸው ግንኙነት ነው ጥንካሬ ውስጣቸው በመሆኑ ስሜት ከፍ ያለ ስለሆነ ምስጥሩ አንድነታችን ሲል ገልጿል።

ለየት ሲላለው የደስታ አገላለፅ ተመስገን ሎሃ ሲመልስ

አዎ የደስታ አገላለጼ በርግጥ ዘንድሮ አዲስ እኔ ብዙ ዋንጫ በልቼ አይቼዋለሁ ምንም አይመስለኝምብዘንድሮ ግን ለምን አዲስ እንዲሆን ካልከኝ ምናልባት ሊጉን ልለቀው ነው መሰለኝ ከ20 ዓመት በታች ከዚህ በኋላ ይበቃኛል የሚል እምነት በውስጤ ስላለ አስቤው አይደለም ድንገት ነው ዘንድሮ የተፈጠረው አዲስ ነገር ስላለ መሰናበቻ ይመስለኛል የእግር ኳስ ስሜት በጣም ጥልቅ ስሜት አለው በተለይ ለኔ ዘንድሮ ደግሞ አዲስ ሆኖብኛል በርግጥ ዋንጫ በልቻለሁ ከ20 ዓመት በታች ለኔ አዲስ አይደለም ወላይታ ድቻ ቤት ለረጅም ዓመት ቆይቻለው ለ9 ዓመት ነው የቆየሁት እና አዲስ አይደለም ግን እንደ አዲስ አሰልጣኝ እየሆንኩኝ ነው እጅግ በጣም ደስ የሚል ጥልቅ ስሜት በጣም እልህ አስጨራሽ ስሜት እንዳለው አብዛኛው የደስታ አገላለፀ ይመሰክረዋል ሲል ገልጿል።

ስለ ሩብ ፍፃሜ ጨዋታ

ከሸገር ከተማ ጋር ቀድሞ ጎል ተቆጥሮብናል ሰዓት ከኛ በተቃራኒው ነበር ወደ 86ኛ ደቂቃ አከባቢ ጎል አስቆጠርን እኔ በወቅቱ ግብ ጠባቂ እና ተጨማሪ ጥሩ የመለያ ምት መቺ የሚባሉ ተጨዋቾችን ልቀይር ነበር ይሄ ጨዋታ ወደ መለያ ምት ይሄዳል ብዬ በመጨረሻም ሁለተኛ ጎል አስቆጠርን ፍፁም የጨዋታው ልዩነት ስለነበረ በቃ ወድቄያለሁ የሚል ተስፋ በውስጤ ነበረ እና ሁለተኛ ጎል ሲቆጠር ደስታዬን ፍፁም መቆጣጠር ስላልቻልኩኝ የእኛን ደጋፊዎች ለማግኘት ሙሉ ሜዳውን መዞር ጀመርኩኝ ሲል በወቅቱ ስለነበረው ሁኔታ ሀሳቡን ገልጿል።

ምናልባት አሰልጣኝነት ከባድ ጫና አለው እና ያንን ውጥረትን እንዴት ልትቆጣጠረው ቻልክ?

ከ20 ዓመት በታች ፕሪምየር ሊግ ውድድር ላይ አሰልጣኝ ሲትሆን ተጫዋቾችን ከማፍራት የዘለሌ ሌላ ነገር ማሰብ አያስፈልግም ዋንጫ ማሸነፍ ሁለተኛ ነገር ነው ዋናው ተጫዋቾችን ለክለቦች ለድቻም ዋናው ክለብ ሆነ ለኢትዮጵያ ክለብ ማብቃቱ ለኔ ከምንም በላይ ነው እና አሰልጣኝነት ጫና አለው አሁን ህዝቡ የሚፈልገው ማሸነፍ ነው በታዳጊዎች ውድድር ቢሆንም ደጋፊው የሚፈልገው ካንተ ማሸነፍ ብቻ ነው ነገር ግን ይሄ የውድድሩ ዓላማ ባይሆንም በጫና ውስጥ ሆነንም የሚፈለገውን ውጤት እያመጣን እንገኛለን በማለት ተናግሯል።

ከተጫዋቾች ጋር ስላለው ግንኙነት በተመለከት

ከተጫዋቾች ጋር ያለው የአባት እና የልጅ ነው ተጫዋቾች እንደ አባት ፣ እንደ ወንድም እና እኔም እንደ ልጄ እንድሁም እንደ ጓደኛ ጭምር ነው እንጂ እንደ አሰልጣኝ አይደለም የሚቀርባቸው አሰልጣኝ የሚሆነው ሜዳ ውስጥ እና ልምምድ ሜዳ ላይ ሳስተምር ነው ከዛ በተረፈ ግን እዝህ ባረፍንበት ማረፊያ ቤት ውስጥ አንድ ቤተሰብ ነን አባታቸው ነኝ እንደ አባታቸው እነሱም ይፈሩኛል እኔም ደግሞ እንደ ልጆቼ እነሱ የተሻለ ቦታ እንዲደርሱ እታተራለሁ እንደዛ አይነት ቅርበት ነው ያለን።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *