በኦሮሚያ ፕሪሚየር ሊግ የሚሳተፈው ጅማ አባ ቡና በኦሮሚያ ሊግ በርካታ አመታትን በአሰልጣኝነት በመስራት የሚታወቀውን እና በኦሮሚያ ሊግ ከዚህ ቀደም ዋንጫ ማንሳት የቻለውን ዮናስ ሙሉጌታ ዋና አሰልጣኝ አድርጎ የሾመ ሲሆን የክለቡ ምክትል አሰልጣኝ በጅማ ከተማ ታዳጊዎች ላይ ለበርካታ አመታት በመስራት የሚታወቀውን ኢዮብ በሀይሉ የክለቡ ምክትል አሰልጣኝ በማድረግ ሾሟል።
ዛሬ በጅማ ከተማ የጅማ አባቡና እግር ኳስ ክለብ ጽ/ቤት በተደረገው የፊርማ ስነ-ስርዓት የተደረገ ሲሆን ታሪካውን ጅማ አባቡና ወደ ቀድሞ ከፍታው ለመመለስ በርካታ ቅድመዝግጅት እንደተደረጉ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል።




