አንተነህ ተስፋዬ ምድረ ገነት ሽረ ክለብ ቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ባደረጉት 17ኛ ሳምንት ጨዋታ በ17ኛ ደቂቃ ላይ ሆን ብሎ በክርን ስለመማታቱ ሪፖርት ቀርቧል ስለሆነም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዲሲፕሊን መመሪያ መሠረት 4 ጨዋታ እንዲቀጣ እና በተጨማሪም ገንዘብ ቅጣት 3000 (ሶስት ሺህ ብር) እንዲከፍል የውድድር ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።
ወልዋሎ ዓድግራት ዩንቨርሲቲ ክለቡ ከሀዲያ ሆሳዕና ጋር ባደረገው 17ኛ ሳምንት ጨዋታ በቅጣት ላይ የነበረ የክለቡ ተጨዋች ጨዋታ ተጠናቆ ዳኞች ከሜዳ ሳይወጡ ወደ ሜዳ አጥሩን ዘሎ በመግባቱም በተጨማሪ ተጨዋቾችን ተከትሎ መልበሻ ክፍል ስለመሄዱ ሪፖርት ቀርቦበታል በመሆኑም ተጨዋቹ ላጠፋው ጥፋት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አክሲዮን ማህበር ለክልሎች ባስተላለፈው መመሪያ መሰረት 25,000 ሺህ ብር ክለቡ እንደከፍል ተወስኗል ።
ሸገር ከተማ ክለቡ 17ኛው ሳምንት መርሃ ግብር ቅድመ ጨዋታ ስብሰባ ላይ ስላለመገኘቱ ሪፖርት ቀርቦበታል ስለሆነም ክለቡ በፈፀመው ጥፋት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የውድድር ደንብ መሰረት 5000 ሺህ ብር እንዲከፍል የውድድር ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።
አሰልጣኝ ስንታየሁ ግድየለው (የሲዳማ ቡና የግብ ጠባቂ አሰልጣኝ) ክለቡ ከነገሌ የአርሲ ጋር በነበረው የ17ኛ ሳምንት ግጥሚያ ጨዋታው ካለቀ በኋላ መልበሻ ክፍል በመሄድ ላይ እያሉ በኮሪደር ላይ ጨዋታ አመራሮችን አጸያፊ ስድብ መሳደባቸው ሪፖርት ቀርቧል ስለሆነም ላጠፉት ጥፋት 6 ጨዋታ እገዳ እና 5000 ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት እንድቀጡ የውድድር አመራር እና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።
ስንታየሁ ወለጬ ምድረ ገነት ሽረ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ባደረገው 17ኛ ሳምንት ጨዋታ በ78 ኛው ደቂቃ ላይ ሁለተኛ ቢጫ ካርድ የሚያሰጥ ጥፋት በመፈፀሙ በቀይ ካርድ ከጨዋታ ሜዳ የተወገደ ስለመሆኑ ሪፖርት ቀርቦበታል ስለሆነም ተጫዋቹ ለፈሰሰው ጥፋት በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት አንድ ጨዋታ እንድቀጣ የውድድር እና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።
ይሁን እንደሻው ከአርባምንጭ ከተማ ፣ ካሌብ አማንኩዋ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፣ ሀብታሙ ጉልላት ከቅዱስ ጊዮርጊስ ፣ ቦና ቦካ ነጌሌ አርሲ ፣ ብሩክ እንዳለ ከወልዋሎ ዓድግራት እና ፍቅረኢየሱስ ተወልደ ብርሃን ከሲዳማ ቡና 5 የቢጫ ማስጠንቀቂያ ካርድ በተለያዩ ጨዋታዎች ተመልክተዋል ስለሆነም ተጨዋቾቹ ለፈፀሙት ጥፋት በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት አንድ ጨዋታ እንድታገዱ እና 1500 ብር የገንዘብ ቅጣት እንድቀጡ የውድድር እና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።
