የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ጨዋታዎችን ከዓመታት በኋላ በአዲስ አበባ ለማካሄድ   ውይይቶች እየተካሄዱ ይገኛሉ!

አዲስ አበባን በመወከል በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ተሳታፊ ከሆኑ ክለቦች ደጋፊዎች ጋር በስፖርታዊ ጨዋታነት ክለቦቻቸው እንዲደግፉ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ እየተካሄደ የሚገኝ ሲሆን የአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ አቶ በላይ ደጀን ከክለብ ደጋፊዎች ጋር ዛሬ ባደረጉት የምክክር መድረክ ላይ  በ2018 ዓ.ም በከተማዋ ደማቅ የእግር ኳስ ውድድር ይከናወናል ብለዋል።

ከኢትዮጵያዊ እሴት ውጪ  የሆኑ ባህሪያት በስፖርቱ መድረክ ሊኖሩ አይገባም ያሉት ኋላፊው  ቢሮው ከደጋፊ ማህበራት ጋር በጋራ ለመስራት ቁርጠኛ መሆኑን አስታውቀዋል።

የኮተቤ ዩኒቨርስቲ ምሁር ወገኔ ዋልተንጉስ (ዶ/ር) በሰጡት የግንዛቤ ማስጨበጫ ውይይት ላይ ደጋፊዎች  ከየክለቦቻቸው ግልፀኝነትና ተጠያቂነት ያሰፈነ አሰራር አለመኖሩ ተከትሎ ቅሬታዎች እንዲበረክቱ አድርጓል ያሉ ሲሆን ወደ ስታዲየም የእግር ኳስ ክለብ ደጋፊ ብቻ ሳይሆን ፣ ለመመልከት ብቻ የሚገቡ ገለልተኛ ተመልካቾች የሚስተናገዱበት መንገድ  መዘርጋት አለበት ሲሉ ተናግረዋል።

Telegram T.me/Dagu_Sport